ዘመናዊ የከተማ ግብርናን ለማስፋፋት በአነስተኛ ቦታ የሚሰሩ የአትክልት እና የፍራፍሬ ስፍራዎች ወሳኝ ናቸው- ወ/ሮ አዳነች

ዘመናዊ የከተማ ግብርናን ለማስፋፋት በአነስተኛ ቦታ የሚሰሩ የአትክልት እና የፍራፍሬ ስፍራዎች ወሳኝ ናቸው- ወ/ሮ አዳነች

አዲስ አበባ፣ ጥር 8፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ዘመናዊ የከተማ ግብርናን ለማስፋፋት በአነስተኛ ቦታ የሚሰሩ የአትክልት እና የፍራፍሬ ስፍራዎች ወሳኝ መሆናቸውን የአዲስ አበባ ከተማ ምክትል ከንቲባ ወይዘሮ አዳነች አቤቤ ገለጹ።

ገበያን በማረጋጋትና የኑሮ ውድነትን ለመቀነስም ከፍተኛ አስተዋጽኦ እንዳለው አስታውቀዋል።

ወይዘሮ አዳነች አቤቤ ዛሬው ዕለት ከትምህርት ሚኒስትር ዶክተር ኢንጂነር ጌታሁን መኩሪያ ጋር በኢትዮጵያ ደረጃዎች ኤጀንሲ የተሰራ ዘመናዊ የከተማ ግብርና ማሳያን ጎብኝተዋል።

ይህን መሰል በአነስተኛ ቦታ የሚሰሩ የአትክልት እና የፍራፍሬ ስፍራዎች ገበያን በማረጋጋትና የኑሮ ውድነትን በመቀነሱ ረገድ ከፍተኛ አስተዋጽኦ ስላላቸው ፣ ዘመናዊ የከተማ ግብርናን ለማስፋፋት ለምንሰራው ስራ እንደተሞክሮ መውሰድ የሚያስችል ሆኖ አግኝተነዋል ብለዋል።

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

The post ዘመናዊ የከተማ ግብርናን ለማስፋፋት በአነስተኛ ቦታ የሚሰሩ የአትክልት እና የፍራፍሬ ስፍራዎች ወሳኝ ናቸው- ወ/ሮ አዳነች appeared first on Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C.

Source: Link to the Post

Leave a Reply