ዘመን ባንክ በበጀት አመቱ በፊት 2.8 ቢሊዮን ያልተጣራ ትርፍ ማግኘቱን ገለጸ።

ይህም ባንኩ በ2015 በጀት አመት 5 ቢሊየን 743 ብር አጠቃላይ ገቢ ያገኘ ሲሆን፣ ከባለፈው አመት ጋር ሲነፃፀር የ1 ቢሊየን ብር 362 ሚሊየን ብር ወይም የ39.7 በመቶ እድገት ማሳየቱን አስታውቋል።

ባንኩ ላስመዘገበው ከፍተኛ ገቢ ከወልድ የተገኘው ገቢ ትልቁን ድርሻ ሲይዝ ይህም 4 ቢሊዮን ብር እንደሚጠጋ ተመላክቷል፡፡

በበጀት አመቱ የገቢና ወጪ ንግድ እንቅስቃሴ መቀነስ የተስተዋለበት ሲሆን የወጪ ንግድ 12 መቶ የቀነሰ ሲሆን የገቢ ንግድ በ6 መቶ ቀንሷል ብሏል ባንኩ።

በሀገራችን ኢኮኖሚ ውስጥ ያለው የውጭ ምንዛሬ አቀቦት መሳሳት እና የግብርና ምርቶች በአለም ገበያ ውስጥ ያላቸው ዋጋ መለዋወጥ እንዲሁም የዓለም ኢኮኖሚ በዋጋ ግሽበት የንግድ ትሥስር መዛባት እና ሌሎች የተለያዩ ምክንያቶች እንደ ችግር ተነስተዋል።

በእሌኒ ግዛቸው
ህዳር 24 ቀን 2016 ዓ.ም

Facebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Source: Link to the Post

Leave a Reply