ዘማሪት ሂሩት በቀለ ከዚህ ዓለም በሞት ተለየች በበፊት የሙዚቃ ህይወቷ ሕይወት እንደሸክላን ጨምሮ በርካታ ድንቅ የሙዚቃ ስራዎችን እንካችሁ ያለችው እና በኋላም በመንፈሳዊ ስራዎች የምትታወቀ…

ዘማሪት ሂሩት በቀለ ከዚህ ዓለም በሞት ተለየች በበፊት የሙዚቃ ህይወቷ ሕይወት እንደሸክላን ጨምሮ በርካታ ድንቅ የሙዚቃ ስራዎችን እንካችሁ ያለችው እና በኋላም በመንፈሳዊ ስራዎች የምትታወቀው ሂሩት በቀለ፣ በአደረባት ህመም በሃገር ውስጥና በውጭ በህክምና ስትረዳ ቆይታ በዛሬው እለት ግንቦት 04 ቀን 2015 ዓ.ም ህልፈተ-ሕይወቷ ተሰምቷል፡፡ ከ1950 መጀመሪያ እስከ 1980ዎቹ መጨረሻ ድንቅ የሙዚቃ ስራዎችን ያስደመጠችን ሂሩት በቀለ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በዘማሪነት/አገልጋይነት ስራዎችን ስትስራ እንደነበር ይታወሳል፡፡ የቀድሞ ድምጻዊት ከዛም ዘማሪት ሂሩት በቀለ በተወለደች በ80 ዓመቷ ነው ከዚህ ዓለም በሞት የተለየችው፡፡ ሂሩት በቀለ የ7 ልጆች እናት፣የ10 ልጆች አያት እና የ7 ልጆች ቅድመ አያት ነበረች።

Source: Link to the Post

Leave a Reply