ዘርን መሰረት በማድረግ ንጹሀንን አማራዎችን ሲያስጨፈጭፉ የነበሩ ከቀበሌ እስከ ክልል ያሉ የቤንሻንጉል ክልል አመራሮችን መንግስት ተጠያቂ ማድረግ እንዳለበት ተገለጸ…

ዘርን መሰረት በማድረግ ንጹሀንን አማራዎችን ሲያስጨፈጭፉ የነበሩ ከቀበሌ እስከ ክልል ያሉ የቤንሻንጉል ክልል አመራሮችን መንግስት ተጠያቂ ማድረግ እንዳለበት ተገለጸ አሻራ ሚዲያ ታህሳስ፡-24/04/13/ዓ.ም ባህር ዳር በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል መተከል ዞን ውስጥ ለተፈጠረው ችግር የህወሃት ጁንታ ተላላኪ በመሆን እጃቸው ያለበት የዞኑ አመራሮች በህግ ተጠያቂ መሆን እንዳለባቸው በዞኑ የሚገኙ የመንግስት ሰራተኞች ጠይቀዋል።… በመተከል ዞን በሁሉም ወረዳዎች የሚሰሩ የመንግስት ሰራተኞች በወቅታዊ ጉዳዮች ዙሪያ በግልገል በለስ ከተማ በወቅታዊ ጉዳዮች ዙሪያ ውይይት አድርገዋል። ሰራተኞቹ በዜጎች ላይ የተፈፀመውን በጭካኔ የተሞላ ግድያ፣ ዘረፋና የንብረት ማውደም ተግባር በፅጽኑ አውግዘዋል። ድርጊቱ በፅንፈኛ ታጣቂዎችና በዞኑ ባሉ የህወሃት ጁንታ ተላላኪ አመራሮች ደጋፊነትና አቀናባሪነት የተከናወነ መሆኑን ጠቅሰው፤ የዞኑ ህዝብ በድርጊቱ ማዘኑን ገልጸዋል። ለጥቃቱ መፈፀም የህወሃት ተላላኪ አመራሮችና ከመንግስት ሰራተኞችም መካከል በቀጥታም ይሁን በተዘዋዋሪ የተሳተፉ እንዳሉ ጠቁመዋል። “እንደ አጠቃላይ በመተከል ዞን ለተፈጠረው ችግር ለጥፋት የሚሰሩ የአመራር አባላት ተሳትፎና ትብብር አለበት” ሲሉም ተናግረዋል። ቀደም ሲል የአገር መከላከያ ሰራዊት በጁንታው ላይ የወሰደውን እርምጃ ለመደገፍ የወጡ ዜጎችን ሲቃወሙ የነበሩ የልዩ ሃይል አባላትና አመራሮች እንደነበሩም አስተያየት ሰጭዎቹ አንስተዋለ። “በዞኑ አመራሩ ለህዝቡ ተጠቃሚነት በትኩረት እየሰራ ባለመሆኑ በርካታ የጉሙዝ እናቶች አሁንም ጫካ ውስጥ ይወልዳሉ” ብለዋል የመንግስት ሰራተኞቹ። ወጣቶች ለጥፋት ቡድኑ በህወሃት እየተመለመሉ አልማሀል ወደሚባል ቦታ ሲወሰዱ የጉሙዝ እናቶች “ልጆቻችን እየተወሰዱ ነው” የሚል ጥያቄ ሲያነሱ የሰማቸው አመራርም እንዳልነበር አስታውሰዋል። በመጨረሻም ዘርን መሰረት በማድረግ ንጹሀንን ሲያስጨፈጭፉ የነበሩ ከቀበሌ እስከ ክልል ያሉ የቤንሻንጉል ክልል አመራሮችን መንግስት ተጠያቂ ማድረግ አለበት ሲሉ በክልሉ የሚገኙ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል፡ ዘጋቢ፡-ጥላሁን ታምሩ

Source: Link to the Post

Leave a Reply