የታሊባን ወታደራዊ ሃይሎች በሰነዘሩት ጥቃት በአፍጋኒስታን ሰሜናዊ ግዛት ኩንዱዝ በምትባል ስፍራ ሁለት የፖሊስ የፍተሻ ስፍራዎች ላይ ጥቃት አድርሰዋል ዘጠኝ የሚሆኑ የፀጥታ ሃይሎችንም ገድለዋል፡፡የግዛቷ አስተዳደሪ አብዱል ሳታር ሚርዛክዋል ትላንት ለአጃንስ ፍራንስ ፕረስ እንደተናገሩት የታሊባን ወታደሮች አመሻሹን በተደጋጋሚ በፖሊስ የፍተሻ ስፍራዎች ላይ ጥቃት ፈፅዋል ብለዋል፡፡ጥቃቱ የተፈፀመባት ግዛት በአሁኑ ሰዓት በመንግስትና በታጣቂ ሃይሎች መካከል ግጭቶችን እያስተናገደች ትገኛለች፡፡
ቀን 08/05/2013
አሐዱ ራዲዮ 94.3
Source: Link to the Post