ዘጠኝ የግብርና ምርቶች ብራንድ ይፋ ተደረገ

ማክሰኞ ጷግሜ 1 ቀን 2014 (አዲስ ማለዳ) በህብረት ሥራ ማህበር አባላት የሚመረቱ የግብርና ምርቶች ብራንድ ይፋ ማድረጊያ አገር አቀፍ ሥነ-ስርዓት በዛሬው ዕለት የተካሄደ ሲሆን፤ በሥነ-ስርዓቱ ላይ ዘጠኝ የግብርና ምርቶች ብራንድ ተደርገዋል።

በኢትዮጵያ ህብረት ሥራ ኮሚሽን አነሳሽነት በኹለተኛ ዙር ብራንድ የተደረጉ የግብርና ምርቶች የአፍዴር ፍየል፣ የቦንጋ በግ፣ የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ለውዝ፣ የሀረር ማንጎ፣ የመቂ ባቱ ሽንኩርት፣ የአፋር ቴምር፣ የሀላባ በርበሬ፣ የአፍዴራ ጨው እና የሶማሌ ቀላፎ ሽንኩርት ናቸው።

የግብርና ምርቶቹን ብራንድ የማድረጉ ፋይዳ ከአገር ውስጥ ገበያ ባሻገር ሰፊ የገበያ መዳረሻዎች እንዲኖራቸው እና በሂደት ምርቶቹ ዓለም አቀፍ ገበያ እንዲያገኙ ለማገዝ እንደሆነ መገለጹን ከኢትዮጵያ ህብረት ሥራ ኮሚሽን ያገኘነው መረጃ አመላክቷል።

የኢትዮጵያ ህብረት ሥራ ኮሚሽን ከዚህ ቀደም የአርባ ምንጭ ሙዝ፣ የጨንቻ አፕል እና የአዊ ድንችን ብራንድ ማድረጉን መዘገባችን ይታወሳል።

Source: Link to the Post

Leave a Reply