You are currently viewing “ዛሬም ወደፊትም የሚደረግ ኢ- ፍትሐዊነት ካለ ያለ አንዳች ክፍያ አብረናችሁ ነን” ጠበቃ #ቤተማርያ አለማየሁ ባህርዳር :-የካቲት 17/2014 ዓ.ም                አሻራ ሚዲያ  ባ…

“ዛሬም ወደፊትም የሚደረግ ኢ- ፍትሐዊነት ካለ ያለ አንዳች ክፍያ አብረናችሁ ነን” ጠበቃ #ቤተማርያ አለማየሁ ባህርዳር :-የካቲት 17/2014 ዓ.ም አሻራ ሚዲያ ባ…

“ዛሬም ወደፊትም የሚደረግ ኢ- ፍትሐዊነት ካለ ያለ አንዳች ክፍያ አብረናችሁ ነን” ጠበቃ #ቤተማርያ አለማየሁ ባህርዳር :-የካቲት 17/2014 ዓ.ም አሻራ ሚዲያ ባልደራስ ለእውነተኛ ዴሞክራሲ ፓርቲ (ባልደራስ) ዛሬ ሐሙስ የካቲት 17 ቀን 2014 ዓ.ም. በዋና ፅ/ቤቱ ለጠበቆቹ ቤተማርያም አለማየሁ፣ ሔኖክ አክሊሉ እና ሶሎሞን ገዛኸኝ የምስጋና መርሃ ግብር አከናውኗል። ጠበቆች ከእውነት ጎን በመቆም ላደረጉት አስተዋፅኦ ፓርቲውና ከፍተኛ አመራሮቹ አመስግነዋል። ድርጅቱ የምስጋና የምስክር ወረቀት አበርክቶላቸዋል። ጠበቃ ቤተማርያም አለማየሁ በመርሃ ግብሩ ላይ ባደረጉት ንግግር “ለብዙ ሰዎች የጥብቅና አገልግሎት ሰጥቻለሁ። ምን ያህል ሰዎች አመስግነውኛል ብየ ሳስብ ሙያው ራሱ ዕድለኛ አይደለም የሚል ድምዳሜ ላይ ደርሼ ነበር። አሁን እርሱን የሚያስቀይር ነገር ነው የተፈጠረው” ብለዋል። እስክንድር ነጋና አቶ ስንታየሁ ቸኮል በፖሊስ መያዛቸውን ከሰሙበት ቅፅበት ጀምሮ ለእነሱ ጥብቅና የመቆም ፍላጎት እንዳደረባቸውም ተናግረዋል። “ለጠበቃ መከፈል የለበትም፤ በነፃ እንከራከራለሁ ብዬ ነው የመጣሁት። ስለተደረገልን ሁሉ አመሰግናለሁ። ዛሬም ወደ ፊትም የሚደረግ ኢ-ፍትሐዊነት ካለ ያለ ገንዘብ ክፍያ ሁልጊዜም አብረናችሁ ነን” በማለትም ጨምረዋል። የባልደራስ የሕግና ሰብዓዊ መብት ሓላፊ ጠበቃ ሔኖክ አክሊሉ በበኩላቸው “ገንዘብ ሊከፈለኝ ሊከፈለኝ አይደለም፤ ከፍየ ብቆም በጣም ደስ ነው የሚለኝ። እነ እስክንድር ለታሰሩበት መዝገብ በመከራከሬ ክብር ይሰማኛል” ብለዋል። “መዝገቡ ለብይን ከተቀጠረ በኋላ ሌላ እጅ ባይገባበት በነፃ ይወጡ እንደነበር ምንም ጥርጥር አልነበረውም። ባልደረቦቼ ቤተማርያምና ሶሎሞን አብረውኝ ችሎት ሲቆሙ የሚሰማኝን ደስታ እኔና ፈጣሪ ነን የምናውቀው። በሙያቸው በእዚህ ደረጃ የሚቆሙ ጠበቆች ማግኘት አስቸጋሪ ነው። ተናበን ሠርተን ጥሩ ውጤት አምጥተናል። ወደፊት የምንሠራውም ብዙ ነው” በማለትም ጨምረዋል። “ለዴሞክራሲ ስንታገል በሀሰት ተከሰስን። አንድ በሕወሓት ጊዜ ለፖለቲካና ለኅሊና እስረኞች ጥብቅና በመቆም የሚታወቁ ጠበቃ ጠይቀን ብዙ ሚሊዮን ብር እንድንከፍላቸው ጠየቁንና ተውነው። እነኝህ ጠበቆች ግን ደሞዝ አልከፈልናቸውም፤ በነፃ ነው የተከራከሩልን። ነገር ግን ልጆቻቸው የሚኮሩባቸው፤ ለኅሊናቸው ያደሩ ጠበቆች ሆነዋል። በኢትዮጵያ ሕዝብ እና በፈጣሪ ስም ከልብ አመሰግናቸዋለሁ” ያሉት ደግሞ ፕሬዚደንት እስክንድር ነጋ ናቸው። የፓርቲው የአደረጃጀት ጉዳዮች ሓላፊው አቶ ስንታየሁ ቸኮል ደግሞ ሦስቱ ጠበቆ ሀሰተኛ ምስክሮችን በመስቀለኛ ጥያቄዎች ያጋለጡበትን ተግባር አድንቀዋል። በመርሃ ግብሩ ላይ የታደሙት የባልደራስ የውጭ ጉዳይ ሓላፊው ሶሎሞን ተሰማ (ዶ/ር) በበኩላቸው ጠበቆቹ ለባልደራስና ለግፍ እስረኞች ላደረጉት ብቻ ሳይሆን ለኢትዮጵያ ላደረጉት አስተዋፅኦ አመስግረዋል። ክሱ ሐሰተኛ መሆኑን ከሕግ አንፃር ያጋለጡት ጠበቆች መሆናቸውን ያስታወሱት ሶሎሞን የኢትዮጵያን ሕዝብ ከተሳሳተ መረጃና ፍረጃ እንዳዳኑትም አብራርተዋል። “በእስር ላይ ያለ ሰው በምርጫ መወዳደር እንደሚችል ያሳዩት እነርሱ ናቸው” ናቸው ሲሉም ገልፀዋል። በመርሃ ግብሩ የተገኙ ታዳሚያንም ጠበቆቹን አመስግነዋል። ለፈጣንና አዳዲስ መረጃዎች የአይበገሬዎቹ ልሳን:- https://www.facebook.com/asharamedia24 ቴሌግራም :- https://t.me/asharamedia24 ዩትዩብ:- https://bit.ly/33XmKro ለፈጣንና አዳዲስ መረጃዎች የአይበገሬዎቹ ልሳን:- https://t.me/asharamedia24 Facebook :- https://www.facebook.com/asharamedia24 ዩትዩብ:- https://bit.ly/33XmKro

Source: Link to the Post

Leave a Reply