ዛሬ በድባጤ የመተከል ታጣቂው ቡድን እንደገና አዲስ የተቀናጀ ጥቃት ከፍቶ ውሏል፡፡ (አሻራ ታህሳስ 20 ፣ 2013 ዓ.ም) በድባጤ ወረዳ በዝግህ ቀበሌ የተደራጁ ታጣቂዎች ዛሬ ጥቃት ከፍተው…

ዛሬ በድባጤ የመተከል ታጣቂው ቡድን እንደገና አዲስ የተቀናጀ ጥቃት ከፍቶ ውሏል፡፡ (አሻራ ታህሳስ 20 ፣ 2013 ዓ.ም) በድባጤ ወረዳ በዝግህ ቀበሌ የተደራጁ ታጣቂዎች ዛሬ ጥቃት ከፍተው…

ዛሬ በድባጤ የመተከል ታጣቂው ቡድን እንደገና አዲስ የተቀናጀ ጥቃት ከፍቶ ውሏል፡፡ (አሻራ ታህሳስ 20 ፣ 2013 ዓ.ም) በድባጤ ወረዳ በዝግህ ቀበሌ የተደራጁ ታጣቂዎች ዛሬ ጥቃት ከፍተው ውለዋል፡፡ በጥቃቱ ስምንት ሰዎች የቆሰሉ ሲሆን፣ ሁለት ሰዎች ደግሞ ህይዎታቸው አልፏል፡፡ ታጣቂው ቡድን ስልጠና እያገኘ እና እንደገና እየተደራጀ እንደሆነ የድባጤ ወረዳ ምስክርናቸውን እየሰጡ ነው፡፡ ዝግህ በተባለች የገጠር ከተማ የተጀመረው ጥቃት ድባጤን ሰላም ነስቷት ውሏል፡፡ የድባጤ ወረዳ አስተዳዳሪ ከሳምንት በፊት ወደ ጫካ የሸፈተ ሲሆን፣ ይያዝ አይያዝ መረጃ አልተገኘም፡፡ የድባጤ ወረዳ አስተዳዳሪ የስድስተኛ ክፍል ተማሪ ሲሆን፣ ምክትሉ ደግሞ ማስተር ዲግሪ በአስተዳድር አላቸው፡፡ ዋናው ጉምዝ ሲሆን፣ምክትሉ ደግሞ ሽናሻ ነው፡፡ በመተከል ይማሩም ፣አይማሩም በመጀመሪያ ስልጣን ለጉምዝ ይሰጣል፡፡ የጉምዝ ባለስልጣናትን አለመማራቸውን በመጠቀም ከውስጥ እስከ ውጭ የሴራ ፖለቲከኞች ለግድያ ይጠቀሙባቸዋል፡፡ የጉምዝ ህዝብ በጠቅላላ 200ሺ ሲሆን 70 ሺው አካባቢ በሱዳን ይኖራል፡፡ የመተከል ህዝብ ደግሞ አጠቃላይ 250 ሺ አካባቢ ሲሆን ከዚህ ውስጥ 50 ከመቶው በአንድ ወር ውስጥ ብቻ ተፈናቅሏል፡፡ የተፈናቀለው ከ100 ሺ እስከ 150 ሺ እንደሚሆን የመተከል የአሻራ ምንጮች ያጠናከሩት መረጃ ያሳያል፡፡ መተከል በተስፋየ ቤልጅጌ እና በጀኔራል አስራት ደኔሮ እንዲረጋጋ የፌዴራል መንግስቱ አመራር ሰጥቷል፡፡ የደቡብ ክልል ተወላጆች አካባቢውን እንዲመሩ የተወከሉ ሲሆን፣ ዓላማውም ከአማራ እና ከኦሮሞ ሽኩቻ ማራቅ እንደሆነ ተሰምቷል፡፡ የኢትዮጵያ ፖለቲካ በአሁኑ ወቅት በአማራ እና በኦሮሞ ሽኩቻ እና በሌሎች አጃቢነት የቆመ ሆኗል፡፡ የፖለቲካ ሁኔታው ምንም ይሁን ምን ግን መፈናቀሉ እና ግድያው በድባጤ ዛሬም ቀጥሎ ውሏል፡፡ መፍትሄ የሚሆነውም ሁሉንም መወከል የሚችል አመራር ሲፈጠር ብቻ እንደሆነ ፖለቲከኞች እየተናገሩ ነው፡፡

Source: Link to the Post

Leave a Reply