ዛሬ የአገልጋይነት ቀን ነዉ!በዚህም መሰረት፡-• የአዲስ አበባ ፐብሊክ ሰርቪስና የሰው ኃይል ልማት ቢሮ እንዳለዉበዛሬው ዕለት የመንግስትና የግል ድርጅት ኃላፊዎች የፅዳት ባለሙያዎችን ተክተ…

ዛሬ የአገልጋይነት ቀን ነዉ!

በዚህም መሰረት፡-

• የአዲስ አበባ ፐብሊክ ሰርቪስና የሰው ኃይል ልማት ቢሮ እንዳለዉ
በዛሬው ዕለት የመንግስትና የግል ድርጅት ኃላፊዎች የፅዳት ባለሙያዎችን ተክተው የጽዳት ስራ ይሰራሉ፡፡

በሁሉም ዘርፍ የተሰማሩ የመንግስት እና የግል ድርጅት ኃላፊዎች በሚመሩት ተቋም ወይም የስራ ዘርፍ ዝቅተኛ የተባለውን ኃላፊነት ተክተው ለግማሽ ቀን አገልግሎት የሚሰጡበት ዘመቻ እንደሚያካሂድ የከተማዋ ፐብሊክ ሰርቪስና የሰው ኃይል ልማት ቢሮ አማካሪ ወ/ሮ መቅደስ ተስፋዬ ተናግረዋል።

የአገልጋይነት ቀን በአዲስ አበባ ከተማ “አገልጋይነት ከእኔ ይጀምራል” በሚል መሪ ቃል የከተማዋ ፐብሊክ ሰርቪስና የሰው ኃይል ልማት ቢሮ አስተባባሪነት ዛሬ እየተከበረ ነው።

• የመንግስትና የግል ትራንስፖርት አገልግሎት ሰጪዎችም ለግማሽ ቀን በነፃ እና ትህትናን በተላበሰ መንገድ ለተሳፋሪዎች አገልግሎት የሚሰጡበት እንዲሁም የግል መኪና አሽከርካሪዎችም ትራንስፖርት ለሚጠብቁ ሰዎችን አገልግሎት የሚሰጡበት እንደሆነ ተናግረዋል።

• የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ ወይዘሮ አዳነች አቤቤ በማኅበራዊ ትሥሥር ገጻቸው ፥ “የአገልጋይነት ቀን”ን ምክንያት በማድረግ ነው የነጻ ትራንስፖርት አገልግሎት እንደሚሰጥ የገለጹት፡፡

በዚህም አዳዲስ የሚሰማሩ አውቶቡሶችን ጨምሮ ፣ ሸገር የብዙኃን ትራንስፖርት አገልግሎት ድርጅትና አንበሳ የከተማ አውቶቡስ አገልግሎት ድርጅት ከጠዋቱ 12 ሰዓት እስከ ምሽቱ 3 ሰዓት ድረስ በነፃ አገልግሎት እንደሚሰጡ ገልጸዋል፡፡
• የአገልጋይነት ቀንን ምክንያት በማድረግ የመንግስት የስራ ኃላፊዎች በመስቀል አደባባይ የፅዳት መረሃ-ግብር በማካሄድ ላይ ናቸዉ፡፡

ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የኢትዮጵያዊያን
ጳጉሜ 04 ቀን 2014 ዓ.ም

ለወቅታዊና ታማኝ መረጃዎች የቴሌግራምና የዩቲዩብ ቻናላችንን ይከታተሉን!

Telegram https://t.me/ethiofm107dot8
YouTube https://www.youtube.com/channel/UCn4D20GPsAtNqN5bIC1BhFA/videos

Source: Link to the Post

Leave a Reply