
#ዛሬ ጠዋት በጸጥታ ኃይሎች ከቢሯቸው የተወሰዱት ዲ/ን ብርሃኑ አድማሱ ተለቀቁ! ግንቦት 14 ቀን 2015 ዓ.ም አሻራ ሚዲያ ፣ ዛሬ ጥዋት ከሥራ ቦታቸው <<ለጥያቄ ትፈለጋለህ>> ተብለው በመንግሥት የጸጥታ ኃይሎ የተወሰዱት ዲ/ን ብርሃኑ አድማሱ መለቀቃቸውን አዲስ ማለዳ አረጋግጣለች፡፡ ዲ/ር ብርሃኑ በአሁኑ ሰዓት ወደ ቢሯቸው መመለሳቸውን አዲስ ማለዳ ያረገጋጠች ሲሆን፤ የጸጥታ ኃይሎች የት ወስደዋቸው እንደነበር ማወቅ አልተቻለም፡፡ ዲ/ን ብርሃኑ የሀገሬ ቴሌቭዥን ሥራ አስኪያጅና በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ውስጥ አሉ ከሚባሉ ታዋቂና ተጽዖኖ ፈጣሪ መምህራን መካከል አንዲ ሲሆኑ፤ ከሰሞነኛው የቤተክርስቲያኗ ወቅታዊ ጉዳይ ጋር በተገኛኘ በማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው ሀሳባቸውን አስፍረው ነበር፡፡ “ውድ የአሻራ ሚዲያ ቤተሰቦች የአሻራ ሚዲያ ቻናልን ላይክና ሰብስክራይብ በማድረግ ድጋፋችሁን ታሳዩን ዘንድ በአክብሮት እንጠይቃለን።” ለፈጣንና አዳዲስ መረጃዎች አሻራ ሚዲያ የአይበገሬዎቹ ልሳን:- // Youtube:- https://www.youtube.com/channel/UCPmgFzP2ZPmdGjHxXjigJaw // Facebook:- https://www.facebook.com/asharamedia24 // ቴሌግራም:- https://t.me/asharamedia24
Source: Link to the Post