ዜሌኒስኪ ከቻይና ጋር መነጋገር እፈልጋለሁ አሉ፡፡የዩክሬኑ ፕሬዝዳንት ቮሎድሚር ዜሌኒስኪ ከቻይናው ፕሬዝዳንት ሺጂፒንግ ጋር በቀጥታ መነጋገር እፈልጋለሁ ማለታቸው ተሰምቷል፡፡መግቢያ እና መውጫ…

https://cdn4.telegram-cdn.org/file/gsm1UDmKhiOjC4aByQ4pihVUQDGZUasEavfapfHf01KtaakcA6BuT3Vq70tA2o9l3c1kErQ4YimYMBY5he32FXjxnl8ybtB2oVL3mBxFXK42gfphNTqy2TrOwVTxbAcEQpv4zgNtYAuFSNmbpo-g7jtcXXbwARDs88cvGH9M15x4mVlZlQJymKRsdMprQITz8L-o3dmhIyQ2Vd3UYw0FpUW-Y54XIGrsLP9v8wCnqvGX8E_Mw0nG8j_5VWWGAD45H98XIhkCsc34Is6CaytpoiSnNQxgIdxYrNx7kTTsGH9nn6PxeCG7qcuJKWCpASyuENKwcY5N7k4UCykzccBw2g.jpg

ዜሌኒስኪ ከቻይና ጋር መነጋገር እፈልጋለሁ አሉ፡፡

የዩክሬኑ ፕሬዝዳንት ቮሎድሚር ዜሌኒስኪ ከቻይናው ፕሬዝዳንት ሺጂፒንግ ጋር በቀጥታ መነጋገር እፈልጋለሁ ማለታቸው ተሰምቷል፡፡

መግቢያ እና መውጫ የጠፋቸው የዩክሬኑ ፕሬዝዳንት ቻይና ምንም አይነት ጦርነት መጀመር የለባትም እና ከፕሬዝዳንቱ ጋር መነጋገር የምፈልገውም ለዛ ነው ብለዋል፡፡

ቤጂንግ ያላትን የኢኮኖሚ እንዲሁም የፖለቲካ የበላይነቷን ማስቀጠል የምትፈልግ ከሆነ ወደ ጦርነት መግባት የለባትም ሲሉ ተናግረዋል፡፡

የጦርነትን አስከፊነት አሁን የተረዱት የሚመስሉት ዜሌኒስኪ ቻይና ጦርነት ማቆም አለባት እያሉ ነዉ፡፡

ከሳውዝ ቻይናው ሞርኒግ ፖስት ጋር ባደረጉት ቆይታ ፕሬዝዳንቱ እንደተናገሩት ሩስያ በሀገራቸው ጦርነት ካወጀችበት እለት አንስቶ እስካሁን ከቻይናው ፕሬዝዳንት ጋር አልተነጋገሩም፡፡

ከሺ ጂፒንግ ጋር በተለያዩ ጊዜያት ለመነጋገር ጥያቄ ያቀረብን ቢሆንም አንድም ቀን አልተሳካልንም ሲሉም ተናግረዋል ዜሌኒስኪ፡፡

ሺ ጂንፒንግ የአለማችን ተጽዕኖ ፈጣሪ የሆነ መሪ ነው እናም የዩክሬንን ጉዳይ ችላ ሊሉ አይገባም ሲሉ በቆይታቸው ተናግረዋል፡፡

በሔኖክ ወ/ገብርኤል
ሐምሌ 28 ቀን 2014 ዓ.ም

Twitter https://twitter.com/EthioFM

YouTube https://www.youtube.com/…/UCn4D20GPsAtNqN5bIC1BhFA/videos

Facebook https://www.facebook.com/onelovebroadcast

ዌብሳይት https://ethiofm107.com/

ያሎትን አስተያየት እና ጥያቄ በአጭር መልዕክት 6321 ላይ ይላኩልን።

ከኛ ጋር ስለሆናችሁ ከልብ እናመሰግናለን።

Source: Link to the Post

Leave a Reply