ዜናዎቻችንን በቀጥታ ይከታተሉ!/////////ከ6፡00-6፡30 በሚቀርበው የምሳ ሰዓት የዜና ሰዓታችን ከምትሰሟቸው ጉዳዮች መካከል፡- -የቁጫ ህዝብ ለዴሞክራሲያዊ ፓርቲ በምርጫ ክልል መንቀሳቀ…

ዜናዎቻችንን በቀጥታ ይከታተሉ!

/////////

ከ6፡00-6፡30 በሚቀርበው የምሳ ሰዓት የዜና ሰዓታችን ከምትሰሟቸው ጉዳዮች መካከል፡-

-የቁጫ ህዝብ ለዴሞክራሲያዊ ፓርቲ በምርጫ ክልል መንቀሳቀስ አልቻልኩም ሲል ቅሬታ አቅርቧል፤

ፓርቲዉ በምንቀሳቀስበት አካባቢ ጥቃቶች በገዥዉ ፓርቲ እየደረሰብኝ ነዉ፤ በዚህም በቀጣይ ለሚካሄደዉ የአካባቢያዊ ምርጫ ለመዘጋጀት ተቸግሪያለሁ ብሏል፤ምርጫ ቦርድ በበኩሉ ስለተባለው ጉዳይ የማውቀው ነገር የለም እያለ ነው፤የፍተሻ ጉዳያችን አድርገነዋል!

-ዓመታዊው የቅዱስ ገብርኤል በዓለ ንግስ በቁልቢ እና በሐዋሳ በድምቀት እየተከበረ ይገኛል፡፡
በቁልቢ በመከበር ላይ በሚገኘው የንግስ በዓል ላይ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ፓትሪያርክ ብጹዕ ወቅዱስ አቡነ ማቲያስ መገኘታቸውም ታውቋል፤ሙሉ መረጃዉን አሰናድተናል!

-ያለ አግባብ ከስራ ተሰናበትን ያሉ የጤና ባለሙያዎች ለጠቅላይ ሚንስትር ጽ/ቤት ደብዳቤ ማስገባታቸው ተነግሯል፡፡
ቅሬታ አቅራቢዎቹ ከ300 በላይ ናቸው ተብሏል፡፡

-በአሜሪካ በተከሰተው ቅዝቃዜ ከ 60 በላይ ሰዎች ህይወታቸው ማለፉ ተሰምቷል፡፡

በሃገሪቱ የተከሰተዉ ከባድ ቅዝቃዜ እና በረዶ ነዋሪዎችን ከተሸከርካሪዎቻቸዉ ዉስጥ እንዳይንቀሳቀሱ አድርጓቸዋል፤የዓለም ጉዳያችን አንዱ ትኩረት ነው፡፡

-ሩሲያ ነዳጇ ከተቀመጠለት የዋጋ ጣሪያ በላይ እንዳይሸጥ ለተስማሙ አገራት የነዳጅ ሽያጭን አላከናውንም ብላለች፤ሆኖም በልዩ ሁኔታ ፑቲን ፈቃድ የሚሰጡበት እድል እንዳለም ተነግሯል፡፡

አድማጮች በዜናዎቻችን እነዚህንና ሌሎችንም ጉዳዮች ትሰማላችሁ፤ዜናዎችን ይዞ አብዱሰላም አንሳር ይጠብቃችኋል!

ለአስተያየትና ጥቆማዎቻችሁ የአጭር የጽሁፍ መልዕክት መቀበያችንን 6321 መጠቀም የምትችሉ መሆኑን ለመጠቆም እንወዳለን፡፡

ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የኢትዮጵያዊያን

Source: Link to the Post

Leave a Reply