ዜና – ሹመት

ዜና - ሹመት

ላለፈው አንድ ዓመት በፕላንና ልማት ሚኒስቴር፣ ሚኒስትር ዴኤታ ሆነው ሲሰሩ የቆዩት አቶ ሳንዶካን ደበበ፤ የጠቅላይ ሚኒስትር ልዩ ጽህፈት ቤት ኃላፊ (chief of staff) ሆነው ተሾሙ። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ፣ በሚኒስትር ዴኤታ ማዕረግ፣ የልዩ ጽህፈት ቤታቸውን እንዲመሩ አቶ ሳንዶካንን የሾሟቸው፤ ከሦስት ሳምንት በፊት መሆኑን ለማወቅ ተችሏል፡፡

በሌላ በኩል፤ ለአዲስ አበባ  ቤቶች ልማትና አስተዳደር ቢሮ የተለያዩ ክፍሎች፣ ሦስት አዳዲስ ሃላፊዎች ተሹመዋል፡፡ ኢንጂነር ስጦታው አካለ፣ በአዲስ አበባ  ቤቶች ልማትና አስተዳደር ቢሮ፣ የቤቶች ልማት ኮርፖሬሽን የግንባታ ዘርፍ ም/ዋና ዳይሬክተር ሆነው የተሾሙ ሲሆን፤ ኢንጂነር ቶማስ ደበሌ፣ በአዲስ  አበባ  ቤቶች ልማትና አስተዳደር ቢሮ፣ የቤቶች ልማት ኮርፖሬሽን የቤት ማስተላለፍ ዘርፍ ም/ዋና ዳይሬክተር ሆነው ተሹመዋል።

አቶ ሙሉነህ ፈይሳ ደግሞ የአዲስ አበባ ቤቶች ልማትና አስተዳደር ቢሮ፣ የቤት ልማትና አሰራር ስርአት ዘርፍ ም/ቢሮ ኃላፊ ሆነው መሾማቸው ታውቋል፡፡

Source: Link to the Post

Leave a Reply