You are currently viewing #ዜና አፈና!! # ሁለት የባልደራስ አባላት ታፍነው አድራሻቸው ጠፋ!! አሻራ ሚዲያ… ሰሜን አሜሪካ  ሁለት የባልደራስ ለእውነተኛ ዴሞክራሲ ፓርቲ (ባልደራስ) አባላት ካለፈው ግንቦት 17…

#ዜና አፈና!! # ሁለት የባልደራስ አባላት ታፍነው አድራሻቸው ጠፋ!! አሻራ ሚዲያ… ሰሜን አሜሪካ ሁለት የባልደራስ ለእውነተኛ ዴሞክራሲ ፓርቲ (ባልደራስ) አባላት ካለፈው ግንቦት 17…

#ዜና አፈና!! # ሁለት የባልደራስ አባላት ታፍነው አድራሻቸው ጠፋ!! አሻራ ሚዲያ… ሰሜን አሜሪካ ሁለት የባልደራስ ለእውነተኛ ዴሞክራሲ ፓርቲ (ባልደራስ) አባላት ካለፈው ግንቦት 17 ቀን 2014 ዓ.ም. ጀምሮ ይህ ዜና እስከተጠናቀረበት ጊዜ፤ ማለትም እስከ ግንቦት 26 ቀን 2014 ዓ.ም. ድረስ የት እንደታፈኑ ማወቅ አልተቻለም። የታፈኑት ወጣቶች ዘገየ በቀለ እና ዳምጤ ተቃጫ ናቸው። ዘገየ ባለፈው የ2013ቱ ሀገራዊ ምርጫ ባልደራስን ወክለው ለአዲስ አበባ የሕግ መወሰኛ ምክር ቤት ከተወዳደሩ ዕጩዎች መካከል አንዱ ሲሆን አዲስ አበባ፤ የካ አባዶ በሚገኘው የአጎቱ መኖሪያ ቤት አቅራቢያ ነው የታፈነው። አጎቱ አቶ ይትረፍ ድንበሩም አብረው እንደታፈኑ የደረሱበት አለመታወቁን ቤተሰቦቻቸው ተናግረዋል። በተመሳሳይ ወጣት ዳምጤ ከ9 ቀናት በፊት ከቤት እንደወጣ አለመመለሱን ቤተሰቦቹ አረጋግጠዋል። ቤተሰቦቻቸው አሁንም ድረስ በየፖሊስ ጣቢያው እየተመላለሱ ቢጠይቁም ሊያገኟቸው አልቻሉም። ምንጭ:- ባልደራስ

Source: Link to the Post

Leave a Reply