
ዜና ዕረፍት የዝዋይ ሐመረ ብርሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን አበምኔት የኔታ ሐረገ ወይን ምሕረቱ በ99 ዓመታቸው ከዚህ ዓለም ድካም አረፉ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ … መጋቢት 2 ቀን 2015 ዓ/ም አዲስ አበባ ሸዋ የኔታ ሐረገ ወይን ከ40 ዓመታት በላይ ወንበር ዘርግተው ያስተማሩ የአቋቋም ሊቅ ሲሆኑ በርካታ ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳትን ጨምሮ ብዙዎችን በዕውቀት ወልደዋል። የኔታ ከብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ተክለ ሃይማኖት ጊዜ ጀምሮ ሁለት ጊዜ ጳጳስ እንዲሆኑ ቢጠየቁም ምንኩስናዬ ይበቃኛል በማለት በዓታቸውን ያጸኑ ታላቅ አባት ነበሩ። በአገልግሎትም ከሀገር ውስጥ እስከ ውጭ ሀገር ፤ከጋሞ ጎፋ አርባ ምንጭ እስከ ኬንያ ኬንያ ፤ከመንበረ ፓትርያርክ የግቢ ኃላፊነት እስከ ዝዋይ ሐመረ ብርሃን ቅዱስ ገብርኤል ገዳም አበምኔትነት ቤተ ክርስቲያን ባሠማራቻቸው ቦታ ሁሉ በቅንነትና በጽናት ያገለገሉ ብዙዎችን በጸሎት የጠበቁ የብዙኃን ጥላና ዋርካ ነበሩ ሲል ተዋህዶ ሚዲያ ማዕከል (ተሚማ) አጋርቷል።
Source: Link to the Post