#ዜና # የኦሮሚያ ልዩ ኃይል ሠላማዊ ሕዝብን በዲሽቃ ተኩስ ደበደበ! ባህርዳር:- መጋቢት 02/2014 ዓ.ም… አሻራ ሚዲያ በምዕራብ ሸዋ ዞን በዳሮ ወረዳ፤ ነዶ…

#ዜና # የኦሮሚያ ልዩ ኃይል ሠላማዊ ሕዝብን በዲሽቃ ተኩስ ደበደበ! ባህርዳር:- መጋቢት 02/2014 ዓ.ም… አሻራ ሚዲያ በምዕራብ ሸዋ ዞን በዳሮ ወረዳ፤ ነዶ ወረዳና ጅባት ወረዳ የሚገኙ ዐማሮች የካቲት 11/2014 ዓ.ም በኦሮሚያ ልዩ ኃይል በድሽቃ፣ በስናይፐርና በሞርታር ተደብድበዋል፡፡ በጥቃቱ አራት ሰዎች እንደሞቱ፣ ከቦታው ተፈናቅለው ደብረብርሃን የገቡ የአካባቢው ነዋሪዎች ገለፁ፡፡ በሶስቱ ወረዳዎች በአስር ሺዎች የሚቆጠሩ ዐማሮች በከተማና በገጠር የሚኖሩ ሲሆን፣ ጠ/ሚ/ር ዐቢይ ሥልጣን በያዙ ማግስት ኦነግ/ሸኔ በአካባቢው መንቀሳቀስ እንደጀመረ ደብረብርሃን የገቡት ተፈናቃዮች ይናገራሉ፡፡ ኦነግ/ሸኔ ወደ አካባቢው መጀመሪያ ሲገባ የታጠቃቸው መሳሪያዎች ብሬን፣ ስናይፐርና ክላሽ የነበሩ ሲሆን፣እስከ ሶስት መቶ ተዋጊዎችን የያዘ ኃይል ሆኖ ይንቀሳቀስ ነበር፡፡ ይህ ኃይል በአካባቢው እንደደረሰ ዐማራን እየለየ እየገደለ፣ እያፈናቀለና ንብረት እያወደመ ቢቆይም ፣ መንግሥት ምንም እርምጃ ባለመውሰዱ፣ የአካባቢው ማህበረሰብ በግል መሳሪያ እየገዛ ራሱን ከመከላከል አልፎ ኦነግ/ሸኔን ለማዳከም ችሎ ነበር፡፡ በዚህ የተቆጡትና በኦሮሚያ ክልላዊ መስተዳድር ያሉት የኦነግ/ሸኔ ሰርጎ ገቦች፣ የኦሮሚያ ልዩ ኃይልን ወደ አካባቢው በመላክ በህዝቡ ላይ ከባድ የቡድን መሣሪያ በሆነው ዲሽቃ ያልታጠቀውን ህዝብ አስመትተውታል፡፡ በዚህ ጥቃት ሰዎች ሞተዋል፣ በርካታ ጉዳትም ደርሷል፡፡ ባልደራስ ለፈጣንና አዳዲስ መረጃዎች የአይበገሬዎቹ ልሳን:- ቴሌግራም :- https://t.me/asharamedia24 Facebook :- https://www.facebook.com/asharamedia24 youtube :- https://www.youtube.com/channel/UChir2nIy58hlLQRYyHIQeHA

Source: Link to the Post

Leave a Reply