You are currently viewing #ዜና ፓርቲያችን ግንቦት 17 ቀን 2014 ዓ.ም ባወጣው ዜና 4 አመራሮቻችንን   በአማራ እና በደቡብ  ክልል ከየሚሠሩበት ቦታ በጸጥታ ኃይሎች ታፍነው ተወስደው የደረሱበትን ማወቅ እንዳልቻል…

#ዜና ፓርቲያችን ግንቦት 17 ቀን 2014 ዓ.ም ባወጣው ዜና 4 አመራሮቻችንን በአማራ እና በደቡብ ክልል ከየሚሠሩበት ቦታ በጸጥታ ኃይሎች ታፍነው ተወስደው የደረሱበትን ማወቅ እንዳልቻል…

#ዜና ፓርቲያችን ግንቦት 17 ቀን 2014 ዓ.ም ባወጣው ዜና 4 አመራሮቻችንን በአማራ እና በደቡብ ክልል ከየሚሠሩበት ቦታ በጸጥታ ኃይሎች ታፍነው ተወስደው የደረሱበትን ማወቅ እንዳልቻልን ገልጸን ነበር። ዜናው በተለያዩ ሚዲያዎች ከተሠራጬ በኋላ ሞጣ አካባቢ በፀጥታ ኃይሎች ታፍነው የነበሩት አቶ ምግባሩ አሥማረ ትናንት አርብ 19/09/2014 ዓ.ም ከቀኑ 11፡00 አካባቢ እንደተለቀቁና ከቤተሰባቸው ጋር እንደተገናኙ ለማወቅ ችለናል፡፡ በሌላ በኩል ወላይታ ሶዶ በቁጥጥር ስር የዋሉት የፓርቲያችን አመራር ወ/ሮ ስመኝ ታደመ እዚያው ሶዶ ከተማ፣ መሐል ከተማ ውስጥ በሚገኝ ፖሊስ ጣቢያ እንዳሉና ከፍተኛ የሐኪም ክትትል የሚፈልገው የጤናቸው ኹኔታ አሳሳቢ እንደሆነ ማወቅ ችለናል፡፡ የኹለቱ አመራሮቻችን ኹኔታ ጥቂት እፎይታ የሰጠን ቢሆንም ከሰቆጣ፣… አቶ ሙሉጌታ የሺጥላ እና ከቲሊሊ፣ አቶ ታደለ ጋሸ የደረሱበትን ለማወቅ ያደረግነው ጥረት እስከአኹን መሳካት አልቻለም፡፡ በሌላ በኩል እኒህ ማሳያዎች እንጂ በየቦታው የሚሳደዱ፣ የሚታፈኑ፣ የሚገደሉ በሺዎች የሚቆጠሩ ንጹሓን ኢትዮጵያውያን ኹኔታ በእጅጉ እያሳሰበን መጥቷል፡፡ ፓርቲያችን በቀን 19/09/2014 ዓ.ም ለብሔራዊ ምርጫ ቦርድ፣ ለኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብት ኮሚሽን፣ ለኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ጉባኤ በደብዳቤ ይህንኑ አሳውቆ በጋራ እየተከታተለ እንደሚገኝ ለማሳወቅ እንወዳለን፡፡ በዚሁ አጋጣሚ በእንዲህ ያለ ወቅት ለታፈኑት ድምጽ የሆናችው የሚዲያ አካላትና ልባም የማኅበረሰብ አንቂዎች ስለበጎ አስተዋጽዖችሁ ልባዊ ምሥጋናችንን ለማቅረብ እንፈልጋለን፡፡ ፓርቲያችን በሕግ ማስከበር ላይ ደጋግሞ የጮኸበትና ፍጹም የማያወላዳ አቋም ያለው ሲሆን እስራቶች ሕጋዊ መንገድን ያልተከተሉ አፈናው ደግሞ ይልቁን ሕገወጥ መሆኑ ከፍተኛ ጥያቄ እንዲያጭርብን ማድረጉን ለማሳወቅ እንወዳለን፡፡ አኹን ያለው የፋኖ አባላትና ቤተሰቦቻቸው፣ በጸጥታ ተቋም ውስጥ ሲሠሩ የነበሩ ባለውለታዎች፣ ጋዜጠኞች፣ የማኅበረሰብ አንቂዎች አግባብ የሌለው አፈና አንዳንዱ በሕግና በሥርዓት የሚፈጸም አብዛኛው ደግሞ ቁጭ ብሎ በመነጋገር መፈታት የሚችሉ ሆኖ ሳለ መንግስት ከድጡ ወደማጡ ዓይነት አካሄዱን በአፋጣኝ እንዲያርም በድጋሚ እናሳስባለን፡፡ ፈጣሪ ሀገራችን ኢትዮጵያንና ሕዝቧን ይጠብቅ እናት ፓርቲ ግንቦት ፳ ቀን ፳፻፲፬ ዓ.ም አዲስ አበባ፣ ኢትዮጵያ አሻራ ሚዲያ ሰሜን አሜሪካ

Source: Link to the Post

Leave a Reply