
#ዜና_እረፍት መምህር ኤፍሬም ሙሉዓለም አርፈዋል! መጋቢት 13 ቀን 2015 ዓ.ም… አሻራ ሚዲያ ፣ ትጉሁና ቀናኢ እንደነበሩ የሚነገርላቸው መምህር ኤፍሬም ሙሉዓለም በባሕር ዳር ሀገረ ስብከት በመንበረ ስብሐት ቅድስት ሥላሴና በደብረ ቅዱሳን አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ቤ/ክ እንዲሁም በተለያዩ ገዳማትና አድባራት ስብከተ ወንጌልን ሲያስፋፉ የነበረ ሲሆን፤ በደረሰባቸው ህመም በባ/ዳር ሀገረ ስብከት አስተባባሪነት የህክምና ገንዘብ ለረጅም ጊዜ ሲሰባሰብላቸው ቆይቶ ወደውጪ ሀገር ሄደው ህክምና የተደረገላቸው ቢሆንም ሳይሻላቸው ወደሀገር ቤት ተመልሰው ዛሬ መጋቢት 13 ቀን 2015 ዓ.ም ከዚህ ዓለም ድካም አርፈዋል። ስርዓተ ፍትሀቱ በባ/ዳር ከተማ ቀበሌ 10 በሚገኘው ደብረ ቅዱሳን አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ቤ/ክ ሲከናወን አድሮ ነገ ሐሙስ ከሌሊቱ 10:00 የአስከሬን ሽኝት ተደርጎ ወደ ትውልድ ቦታቸው ከወተት ዓባይ ከተማ በስተደቡብ 10 ኪ.ሜ ርቀት በምትገኘው ዳጊ ከተማ ዳጋሊ ቅዱስ ሚካኤል ቤተ ክርስቲያን ስርዓተ ቀብራቸው እንደሚፈፀም ተገልጿል። “ውድ የአሻራ ሚዲያ ቤተሰቦች የአሻራ ሚዲያ ቻናልን ላይክና ሰብስክራይብ በማድረግ ድጋፋችሁን ታሳዩን ዘንድ በአክብሮት እንጠይቃለን።” ለፈጣንና አዳዲስ መረጃዎች አሻራ ሚዲያ የአይበገሬዎቹ ልሳን:- // Youtube:- https://www.youtube.com/channel/UCPmgFzP2ZPmdGjHxXjigJaw // Facebook:- https://www.facebook.com/asharamedia24 // ቴሌግራም:- https://t.me/asharamedia24
Source: Link to the Post