ዜጎችን ከሳዑዲ አረቢያ የማስመለሱ ዕቅድ ተጠናቀቀ – ውጭ ጉዳይ ሚ/ር

https://gdb.voanews.com/01000000-0aff-0242-f040-08db35457106_tv_w800_h450.jpg

የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር፣ በአንድ ዓመት ውስጥ 131 ሺሕ ኢትዮጵያውያንን ከሳዑዲ አረቢያ ማስመለሱን አስታወቀ፡፡ በችግር ላይ የወደቁ እና በሳዑዲ እስር ቤቶች የቆዩ ኢትዮጵያውያንን ወደ አገር ቤት ሲመልስ የቆየው ብሔራዊ አስመላሽ ኮሚቴ፣ የአንድ ዓመት ዕቅዱን ማጠናቀቁን፣ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ብርቱካን አያኖ ተናግረዋል፡፡

ለአንድ ዓመቱ በተያዘው ግብ መሠረት፣ የመጨረሻዎቹ ተመላሾች፣ በሦስት በረራዎች፣ በትላንትናው ዕለት ወደ ዐዲስ አበባ ገብተዋል፡፡ በሳዑዲ አረቢያ ብዙ ሥቃይ እንደ ደረሰባቸው የተናገሩት ተመላሾቹ፣ አሁንም በተለያዩ እስር ቤቶች የሚሠቃዩ በርካታ ኢትዮጵያውያን መኖራቸውንና መንግሥት እንዲደርስላቸው ጥሪ አቅርበዋል፡፡

ሙሉ ዘገባውን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።

Source: Link to the Post

Leave a Reply