ዝምተኛው ፓትርያርክ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆሬዎስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ

እጣ ክፍሉ ነው እና መርቆሬዎስ ሲፈጠር
ይቺን አለም ተጸይፎ በአርምሞ ነው የሚኖር

Image may contain: one or more people and beardዝምተኛው ፓትርያርክ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆሬዎስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ እንኳን ለ32ኛ ዓመት በዓለ ሲመትዎ አደረሰዎት !

…ዓለምን በአርምሞ ያስደመሙት ብጹእ ወቅዱስ አባታችን የስማቸው ትርጉዋሜ መርቆሬዎስ ማለት የአብ ወዳጅ የወልድ አገልጋይ ማለት ነው።

አረመመ ማለት ጸጥ አለ፣ ዝም አለ ማለት ነው፡፡ አንድ ሰው አንደበቱን ከንግግር ገትቶ፣ ራሱን በጸሎት አበርትቶ የሚቆይበት ጊዜ አርምሞ ይባላል፡፡ አርምሞ ከሱባኤ ጋር የተያያዘ ነው፡፡ በሱባኤ መነጋገር የማንችልበትን የዝምታና የጸጥታ፣የጥሞና ጊዜ ነው አርምሞ የምንለው፡፡

የአርምሞ ሕይወት በየገዳማቱ የሚኖሩ ዝጉሃውያን አባቶቻችንና እናቶቻችን ይኖሩታል፡፡ ይህም ከሰው ጋር በአንደበታቸው የማያወሩበት ከእግዚአብሔርና ከእመቤታችን እንዲሁም ከቅዱሳን ጋር በጸሎት የሚነጋገሩበት የሰላምና የዝምታ ወርቃማ ሕይወታቸው ነው፡፡

የአርምሞ ሕይወት ከየትኛውም መንፈሳዊ ሕይወት እጀግ ከባድ ቢሆንም ሰላምና ጸጥታ ተመስጦን የተሞላ ስለሆነ ከትልቅ ጸጋና ማዕረግ የሚያደርስ ነው፡፡ ማንም ሰው ይህንን ሕይወት ለመኖር አይችልም፡፡ ከእግዚአብሔርና ከእናቱ ከድንግል ማርያም ካልተሰጠው በቀር፡፡

በብሉይ ኪዳን የነበሩት አባቶችና ነብያት፣ በአዲስ ኪዳንም ሐዋርያት ይህንን ሕይወት በጾም ወቅት በስፋት ኖረዋል፡፡ ጌታችንም በቆሮንጦስ ገዳም የያዘው ሱባኤ በአርምሞ ነው፡፡ አንድም ሐዋርያት አጠገቡ ወይንም አብረውት አልነበሩም፡፡

በብዙ ገድለ ቅዱሳን ላይ ቅዱሳን በተለይ በጾም ወቅት በጸሎት ጥሙድ እንደ በሬ፣ ትጉህ እንደ ገበሬ ሆነው በአርምሞ ይሰነብታሉ፡፡ በዚህም ከፈጣሪ ጋር ብቻ በመነጋገር ከሰው ጋር በማርመም ብዙ ቃልኪዳን ተቀብለዋል፡፡
Zelalem Tsegaye

Source: Link to the Post

Leave a Reply