ዝግጅቴን አጠናቅቂያለሁ….ምርጫ ቦርድ!በደ/ብ/ብ/ሕ ክልላዊ መንግሥት በሚገኙ ስድስት ዞኖች (ኮንሶ፣ ደቡብ ኦሞ፣ ዎላይታ፣ ጋሞ፣ ጌዴኦ፣ ጎፋ) እና አምስት ልዩ ወረዳዎች (ቡርጂ፣ ባስኬቶ፣…

ዝግጅቴን አጠናቅቂያለሁ….ምርጫ ቦርድ!

በደ/ብ/ብ/ሕ ክልላዊ መንግሥት በሚገኙ ስድስት ዞኖች (ኮንሶ፣ ደቡብ ኦሞ፣ ዎላይታ፣ ጋሞ፣ ጌዴኦ፣ ጎፋ) እና አምስት ልዩ ወረዳዎች (ቡርጂ፣ ባስኬቶ፣ አሌ፣ አማሮ፣ ዲራሼ) ህዝበ ዉሳኔ ለማካሄድ ዝግጅቱን ማጠናቀቁን ምርጫ ቦርድ ገለፀ።

የኢትዮጵያ ብሄራዊ ምርጫ ቦረድ በ16 ቀናት ዉስጥ የመራጮች ምዝገባ በመደበኛ ምርጫ ጣቢያዎች እና በተፈናቃይ ምርጫ ጣቢያዎች ምዝገባ ተከናዉኖ ያለቀ ሲሆን የመራጮች መመዝገቢያ ጣቢያዉ ለህዝብ ይፋ ተደርጓል ተብሏል።

ከ1500 በላይ መራጭ ለመመዝገብ 9 ንዑስ ምርጫ ጣቢያ የተጨመረ ሲሆን በ24 ምርጫ ጣቢያዎች በተፈጠረ የህግ ጥሰት የምርጫ አስፈፃሚዎች ተቀይረዉ እና አዲስ አስፈፃሚዎች ተመርጠው እስከ ጥር 3 ቀን 2015 ዓ.ም የመራጮች ምዘገባ እየተካሄደ እንደሚቆይ ተገልጿል።

የምርጫ ቦርድ በ3 ሺህ 769 ምርጫ ጣቢያዎች ላይ 2 ሚሊዮን 934 ሺህ 143 ሰዉ የተመዘገበ ሲሆን 525 አካል ጉዳተኞችም ይገኙበታል ተብሏል።

የድምፅ መስጫ ወረቀቱ ላይ የሚያርፉ ምልክቶችም የተመረጡ ሲሆን በህዝበ ዉሳኔዉ መሠረት በአንድ ክልል መደራጀት እፈልጋለሁ ለሚሉ “ነጭ እርግብ” እንዲሁም በአንድ ክልል መደራጀቱን አልደግፍም ለሚለዉ የህብ ዉሳኔ አማራጭ ደግሞ “የጎጆ ቤት” ምልክት እንዲሆን መመረጡን የምርጫ ቦርድ ሰብሳቢዋ ብርቱካን ሚዴቅሳ ገልፀዋል።

ጥር 29 ቀን 2015 የሚደረገዉን ህዝበ ዉሳኔ በታዛቢነት ለመሳተፍ ፍላጎት ያላቸዉን የሲቪል ማህበረሰብ መስፈርቱን ላሟሉ የሲቪል ማህበራት ድርጅቶች ዕዉቅና መሰጠቱን የገለፁት የምርጫ ቦርድ ዋና ሰብሳቢ ብርቱካን ሚደቅሳ 5 ሺህ 274 ታዛቢዎች እንደሚሳተፉም ገልፀዋል።

በመራጮች ምዝገባ ሂደት ኢ.ሰ.መ.ኮን ጨምሮ 117 ታዛቢዎችና 17 ሰብአዊ መብት ተቆጣጣሪዎች በመስክ ላይ እንደሚገኙም ጨምረው ገልጸዋል።

በአቤል ደጀኔ
ጥር 01 ቀን 2015 ዓ.ም

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ወቅታዊ አዳዲስ መረጃዎችና ፕሮግራሞችን ለማግኘት ከታች ያሉትን ገፆቻንን ይጎብኙ ቤተሰብ ይሁኑ ።

Telegram https://t.me/ethiofm107dot8

Twitter https://twitter.com/EthioFM

YouTube https://www.youtube.com/…/UCn4D20GPsAtNqN5bIC1BhFA/videos

Facebook https://www.facebook.com/onelovebroadcast

Website https://ethiofm107.com/

ያሎትን አስተያየት እና ጥያቄ በአጭር መልዕክት 6321 ላይ ይላኩልን።
ከኛ ጋር ስለሆናችሁ ከልብ እናመሰግናለን።

Source: Link to the Post

Leave a Reply