You are currently viewing የሀረሪ ክልል ውሃና ፍሳሽ አገልግሎት ባለስልጣን 25 ሚሊየን ብር የሚያወጡ አምስት የውሃ ቦቴዎችን ተረከበ

የሀረሪ ክልል ውሃና ፍሳሽ አገልግሎት ባለስልጣን 25 ሚሊየን ብር የሚያወጡ አምስት የውሃ ቦቴዎችን ተረከበ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 28፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የሀረሪ ክልል ውሃና ፍሳሽ አገልግሎት ባለስልጣን 25 ሚሊየን ብር የሚያወጡ አምስት የውሃ ቦቴዎችን ከክልሉ ርዕሰ መስተዳደር አቶ ኦርዲን በድሪ ተረከበ፡፡
የውሃ ቦቴዎቹ ከከተማ ተቋማት እና መሰረተ ልማት ማስፋፊያ ፕሮግራም የሀረር ከተማ ፕሮጀክት ማስተባበሪያ ፅህፈት ቤት የተገኘ መሆኑ ታውቋል፡፡
በርክክብ መርሃግብሩ አቶ ኦርዲን በድሪ የክልሉ የመጠጥ ውሃ ችግርን ለመቅረፍ ከተለያዩ አካላት ጋር በመቀናጀት እየተሰራ መሆኑን ገልፀዋል።
በሌላ በኩል የክልሉን የውሃ ችግር ለመፍታት የረጅም ጊዜ እቅድ ይዞ መስራት ቢያስፈልግም ለግዜው ያለውን ችግር በፍትሃዊነት መፍታት ያስፈልጋል ማለታቸውን ከሀረሪ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ቢሮ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡-https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

The post የሀረሪ ክልል ውሃና ፍሳሽ አገልግሎት ባለስልጣን 25 ሚሊየን ብር የሚያወጡ አምስት የውሃ ቦቴዎችን ተረከበ appeared first on Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C.

Source: Link to the Post

Leave a Reply