የሀረር ቀን አብሮነትና ወንድማማችነትን በሚያጠናክር መልኩ እንደሚከበር የበዓሉ ኮሚቴ ገለጸ፡፡

የዘንድሮው 26ኛው ዓለም አቀፍ የሀረር ቀን አብሮነትና ወንድማማችነትን በሚያጠናክር መልኩ እንደሚከበር ነው የበዓሉ አብይ ኮሚቴ ያስታወቀው።

የኮሚቴው ሰብሳቢና የሀረሪ ብሔራዊ ጉባኤ አፈ ጉባኤ ሙህየዲን አህመድ በክልሉ በዓሉን የሚመጥን ዝግጅት ሲደረግ መቆየቱን ጠቁመው በአሁኑ ወቅት በዓሉን በተሳካ ሁኔታ ለማክበር የሚያስችል ዝግጅት መደረጉን ገልጸዋል።

“ሀረር የሰላም፣ የመቻቻልና የአብሮነት ተምሳሌት” በሚል መሪ ቃል በሚከበረው በዓል ለመሳተፍም ከተለያዩ የዓለም ክፍሎች እንግዶች ወደ ክልሉ እየገቡ መሆኑ ተነግሯል፡፡

ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የኢትዮጵያዊያን

ሰኔ 25 ቀን 2016 ዓ.ም

Facebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Source: Link to the Post

Leave a Reply