
የሀያላኑ ሀገራት ፍጥጫ ሲቀጥል ቻይና ከአሜሪካ ገበሬዎች በቆሎ መግዛቷን እንደምታቆም ገለጸች። ግንቦት 07 ቀን 2015 ዓ.ም አሻራ ሚዲያ ፣ እንደ ብሉምበርግ ዘገባ ከሆነ ቻይና ከአሜሪካ ገበሬዎች የበቆሎ ምርት በመግዛት ቀዳሚ ሀገር ስትሆን በቀጣል ላትገዛ እንደምትችል ገልጻለች። ቻይና ባለፉት ሁለት ሳምንት ውስጥ ብቻ 832 ሺህ ቶን የበቆሎ ምርት የመግዛት እቅዷን ሰርዛለች። ቤጂንግ ከዚህ ውሳኔ ላይ የደረሰችው ከብራዚል በመግዛቷ ነው ተብሏል። የብራዚል በቆሎ ምርት ከአሜሪካው ጋር ሲነጻጸር በዋጋ እና በትራንስፖርት ቅናሽ ማሳየቱ የተገለጸ ሲሆን የቻይናን ውሳኔ ተከትሎም የአሜሪካ በቆሎ አምራች ገበሬዎችን እንዳሳሰባቸው ተገልጿል። “ውድ የአሻራ ሚዲያ ቤተሰቦች የአሻራ ሚዲያ ቻናልን ላይክና ሰብስክራይብ በማድረግ ድጋፋችሁን ታሳዩን ዘንድ በአክብሮት እንጠይቃለን።” ለፈጣንና አዳዲስ መረጃዎች አሻራ ሚዲያ የአይበገሬዎቹ ልሳን:- // Youtube:- https://www.youtube.com/channel/UCPmgFzP2ZPmdGjHxXjigJaw // Facebook:- https://www.facebook.com/asharamedia24 // ቴሌግራም:- https://t.me/asharamedia24
Source: Link to the Post