የሀገራችን አዳር (ታህሳስ 23፣ 2013ዓ.ም) 1)  በአውሮፓውያኑ በቄስ ጎርጎርዮስ የዘመን ቀመር ዘመናቸውን የሚያሰሉ ዓመታቸውን ቀይረው አድረዋል፡፡ ዓመቱ 2021 ሆኗል፡፡ የአፍሪካ ህብረ…

የሀገራችን አዳር (ታህሳስ 23፣ 2013ዓ.ም) 1) በአውሮፓውያኑ በቄስ ጎርጎርዮስ የዘመን ቀመር ዘመናቸውን የሚያሰሉ ዓመታቸውን ቀይረው አድረዋል፡፡ ዓመቱ 2021 ሆኗል፡፡ የአፍሪካ ህብረ…

የሀገራችን አዳር (ታህሳስ 23፣ 2013ዓ.ም) 1) በአውሮፓውያኑ በቄስ ጎርጎርዮስ የዘመን ቀመር ዘመናቸውን የሚያሰሉ ዓመታቸውን ቀይረው አድረዋል፡፡ ዓመቱ 2021 ሆኗል፡፡ የአፍሪካ ህብረት አዲሱ ዓመት ለአፍሪካ የተሻለ ሰላም የሚመዘገብበት እንዲሆን ተመኝቷል፡፡ 2) ሱዳን ከኢትዮጵያ ስትጠይቅ የነበረውን ድንበር ሙሉ በሙሉ መቆጣጠሯን ማታ በይፋ ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥታለች፡፡ ሱዳናውያን የክፍለዘመናቸው ድል አድርገው ወስደውታል፡፡ ከወደ መተማ አካባቢ በምሽቱ እንደተሰማው ዜና ደግሞ ሌሊቱን የሱዳን ጦር ወደ ኢትዮጵያ ከ 30 ኪሜ በላይ ዘልቆ ገብቶ ምሽግ እየቆፈረ ነው፡፡ ወደ መተማም ተጠግቷል፡፡ ሱዳን የኢትዮጵያ አርሶአደሮች የወረሩትን ቦታ ሙሉ በሙሉ አስመልሻለሁ ብላለች ሲል አልጀዚራ ዘግቧል፡፡ ኢትዮጵያ በበኩሏ ከሱዳን ጋር ሰላም እሻለሁ፣ ችግሬን በዲፕሎማሲ እፈታለሁ እያለች ነው፡፡ ሱዳን ግን በርካታ መሬቶችን ከተቆጣጠርኩ በኃላ ዲፕሎማሲው ይቀጥላል ስትል እየተናገረች ነው፡፡ እስካሁን ወደ 3 ሺ ኢትዮጵያን በሱዳን መስፋፋት ምክንያት የተፈናቀሉ ሲሆን፣ ከ1.5 ቢሊየን ብር በላይ ንብረትም በሱዳን ተዘርፏል፡፡ ወድሟል፡፡ 3) ግብፅ ኢትዮጵያን በሱዳን ወረራ ጉዳይ ስሜን ያላግባብ እያጠፋሽ ነው ያለቻት ሲሆን፣ ኢትዮጵያ በበኩሏ ስምሽን የጠራ ማንም የለም ስትል ምላሽ ሰጥታለች፡፡ ግብፅ ከኢትዮጵያ ጋር ጠብ ያማራት ይመስላል፡፡ የኢትዮጵያ የዲፕሎማሲ ሁኔታም ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተበላሸ ሂዷል፡፡ 3) ብልፅግና ፓርቲ የሀገሪቱን ሁኔታ የገመገመበት ሁኔታ ፈፅሞ የኢትዮጵያን ችግር ሊፈታ የማይችል እንደሆነ አሻራ ሰነዱን መርምሮ ተረድቷል፡፡ ብልፅግና ስለ መፈናቀል እና ስለ ሀገር ሉዓላዊነት ሳይወያይ እርስ በእርሱ ሲሻኮት ከርሟል፡፡ የብልፅግና ሰነድም ሁሉም የብልፅግና ክንፎች የአማራ ብልፅግናን እና ህዝብን በሚተች መንገድ የተዘጋጀ ነበር፡፡ ይሄን የተመለከቱ ፀጋ አራጌ የተባሉ የአማራ ብልፅግና አባል ከብልፅግና ጋር አማራ መቀጠል የለበትም ያሉ ሲሆን፣ አብይ አህመድ መነጠል ትችላላችሁ የሚል ሀሳብ አንስተዋል፡፡ አብይ አህመድ ወጥ አቋም የሌላቸው፣ የበዛ ስሜታዊነት የሚንፀባረቅባቸው፣ ሰነፍ በመሰብሰብ ራሳቸውን ንጉስ ማድረግ የሚፈልጉ እና የሀገሪቱን ውስብስብ ችግር ተረድተው ዘላቂ መፍትሄ ከማዘጋጀት ይልቅ ለታይታ ስራ የሚሮጡ መሪ እንደሆነ ብልፅግናዎች ይመሰክራሉ፡፡ በአብይ አህመድ ዴሞክራሲ ይመጣል ተብሎ አይታሰብም የሚሉም ብዙ ናቸው፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትሩ መለስ ዜናዊን፣ የኦሮሞ ብልፅግና ደግሞ ህወኃትን ለመሆን ቢጥሩም የተለመደ መንገድ ስለሆነ አዋጭ ሚሆንላቸው አይመስልም፡፡፡ አመራሩም ህዝቡም ነቅቷል፡፡ 4) ሰሞኑን ሁሉም የብልፅግና ክልላዊ ክንፎች ስለ ወቅታዊ ሁኔታ ሰነድ አዘጋጅተው ግምገማ እያደረጉ ሲሆን፣ የግምገማቸው መዳረሻ እርስ በእርስ መካሰስ እንደሚሆን ከወጣው ሰነድ መረዳት ይቻላል፡፡ የቢሻንጉል ብልፅግና በነሽመልስ አብዲሳ የቆመ ስለሆነ የኦሮሚያ ክልል ብልፅግና የተሻለው ብልፅግና ነው፣ ሰላምም አምጥቷል ሲል በሰነዱ ገምግሟል፡፡ የኦሮሚያ ብልፅግና በአሶሳ ፅህፈት ቤት ከፍቶ ቢሻንጉል የጋራችን ነው እያለ ሲሆን ካማሺ ዞን ያሉ ወረዳዎችን ወደ ወለጋ እያጠቃለለም ይገኛል፡፡ የኦነግ ጦር ደግሞ መተከል ድባጤ ወረዳን እያመሳት ነው፡፡ ኦነግ በቢሻንጉል የራሱ ፅህፈትቤት ያለው ሲሆን፣ የቢሻንጉል አመራሮች ሁሉም ያሸነፈ መስሎ ለታያቸው ሁሉ ስለሚወግኑ በአሁኑ ወቅት ሽመልስ አብዲሳን እየደገፉ ነው፡፡ የአማራ ብልፅግናዎች ከወሬ ውጭ የተጨበጠ ስራ መስራት አልቻሉም፡፡ የአማራ ምሁራን መማክርት የሚባለው ጥገኛ ቡድንም ብአዴንን የበለጠ እያጃጃለው ይገኛል ፡፡ በምሁራን መማክርቱ የመጡ ሁሉም አመራሮች ወቅታዊ ሁኔታውን የሚረዱ አይደሉም፡፡ 5) ሁሉም የሀገራችን ሚዲያዎች ከታህሳስ 22 ጀምሮ ከናይል ሳት ወርደው ወደ ኢትዮ ሳት ይገባሉ ቢባልም ብሮድካስትጠባለስልጣን ያልጨረስኩት ጉዳይ አለ ብሎ ለተወሰነ ቀናት እንደዘገ ለማወቅ ተችሏል፡፡ 6) መተከል አልተረጋጋም፡፡ ሰባዊ ድጋፍ ለማድረግ አሽከርካሪዎች ሊገቡ አልቻሉም፡፡ ርሃብ እና ጦርነት በመተከል አሁንም እንዳለ አለ፡፡ መተከል እንዳይረጋጋ እና አማራውን በማስወጣት ኦሮሞ ለማስፈር እነ ሽመልስ አብዲሳ እየሰሩ ነው እየተባለም ነው፡፡ ሀገራችንን በእውነተኛ መረጃ ነቅተን እንጠብቅ! ሰናይ ውሎ!

Source: Link to the Post

Leave a Reply