የሀገራዊ ምክክር ሂደቱ”ችግሮችን በዘላቂ ሁኔታ ለመፍታት እንጂ ለጊዜው የሚደረግ ተግባር እንዳይሆን መጠንቀቅ ያስፈልጋል”—ፕሬዝዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ ሀገራዊ የ…

የሀገራዊ ምክክር ሂደቱ”ችግሮችን በዘላቂ ሁኔታ ለመፍታት እንጂ ለጊዜው የሚደረግ ተግባር እንዳይሆን መጠንቀቅ ያስፈልጋል”—ፕሬዝዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ

ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ ሀገራዊ የምክክር መድረክ አስፈላጊ ነቱ “ችግሮችን በዘላቂ ሁኔታ ለመፍታት እንጂ ለጊዜው የሚደረግ ተግባር እንዳይሆን መጠንቀቅ አስፈላጊ ነው ብለዋል።

ፕሬዚዳንቷ በሀገራችን ተጨባጭ ሁኔታ የሃሳብ ልዩነት እያደረስብን ያለው ኪሳራ ትልቅ በመሆኑ ይህ መድረክ የሚኖረው ጠቀሜታ ላቅ ያለ መሆኑንም አመላክተዋል።

ፕሬዘዳንቷ ይህን የተናገሩት በዛሬው ዕለት በሀገራዊ የምክክር ሂደቱ የሴቶች ተሳትፎና ድርሻ ምን መሆን አለበት በሚል በተካሄደ ውይይት ላይ ነው፡፡

በኢትዮጵያ ሀገራዊና እጅግ መሰረታዊ በሆኑ ጉዳዮች ላይ የሀሳብ ልዩነቶች ወይንም አለመግባባቶች መኖራቸውን አንስተው ፣እነዚህን የሀሳብ ልዩነቶች ወይም አለመግባባቶች እንደ ምክክር ባሉ ሰላማዊ አማራጮች ከመፍታት ይልቅ የሃይል አማራጮች ጥቅም ላይ ሲውል ይስተዋላልም ነው ያሉት።

በመሆኑ በሀገራችን ግማሽ ያህሉን የህዝብ ቁጥር የሚይዙት ሴቶች ውሳኔ በሚሰጥባቸው ቦታዎች ላይ መኖር ለአገር ጥቅሙ ብዙነው ብለዋል፡፡
ፕሬዚዳንቷ ሴቶች በሀገር ጉዳይ ላይ በየትኛውም መስክ ከወንዶች እኩል ድምፃቸውን ማሰማት መብታቸው ነው፣ በመሆኑ እኩል ንቁ ተሳትፎ እንዲያ ደርጉ እንጂ ለቁጥር ወይም ለኮታ ማሟያ መሆን የለበትም ብለዋል፡፡

የሴቶች እና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር ኤርጎጌ ተስፋዬ በበኩላቸው፣ በምክክሩ የሴቶች ድርሻ መኖሩ በከፍተኛ ሁኔታ የአገረ መንግስት ግንባታ ይፋጠናል፣ ዘላቂ ሰላምም እንዲሰፍን ጉልህ ሚና አለው፣ ለዚህም የሌሎች ሀገራት ተሞክሮን ማየት ተገቢ ነው ብለዋል፡፡

የአገራዊ ምክክር ኮሚሽን ኮሚሽነር ፕሮፌሰር መስፍን አርአያ በበኩላቸው፣ የምክክሩ ሂደት የሴቶች ሚና ከፍተኛ በመሆኑ በዚህ ሀገራዊ የምክክር መድረክ ተሳታፊዎች 30 በመቶው የሚሆኑት ሴቶች ናቸው ብለዋል፡፡
በምክክሩ ሴቶች በንቃት የሀሳብ ተሳትፎ እንዲያደርጉ የተለያዩ የግንዛቤ ማስጨበጫና ድጋፍ እያደረግን፣ በምክክር መድረኩ ሴቶች ድምፃቸው ጎልቶ የሚሰማበት እንዲሆን እየሰራን ነው ብለዋል፡፡

በልዑል ወልዴ

ሚያዝያ 19 ቀን 2016 ዓ.ም

Source: Link to the Post

Leave a Reply