የሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን አባላት የተመረጡበት መንገድ ላይ ቅሬታ እንዳላቸው ተፎካካሪ የፖለቲካ ፓርቲዎች ገለጹ

https://gdb.voanews.com/023d0000-0aff-0242-fe49-08da0852bdf4_tv_w800_h450.jpg

ለአሜሪካ ድምፅ አስተያየታቸውን የሰጡት የኦፌኮ፣ የአረና እና የኢዜማ አመራሮች፣ የኮሚሽኑ አባላት የተመረጡበት አካሔድ አካታች እንዳልሆነ እና አሁን በተያዘው መንገድ ውጤታማ መሆን ይቻላል ብለው እንደማያምኑ ገልጸዋል፡፡

የኮሚሽኑ ሰብሳቢ ፕሮፌሰር መስፍን አርዓያ በበኩላቸው በኮሚሽኑ ማቋቋሚያ አዋጅ መሰረት እንደተመረጡ ገልጸው ፍላጎት ያለው አካል ሁሉ በኮሚሽኑ የሥራ ሂደት እንደሚሳተፍ ተናግረዋል፡፡

የኮሚሽኑ ዓላማ ሕዝቡ የሚፈልጋቸውን አጀንዳዎች በመለየት ሁሉም የሚወያይበትን ሁኔታ ማመቻቸት ብቻ እንደሆነም አመልክተዋል፡፡

Source: Link to the Post

Leave a Reply