የሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን የመሰሉ የንግግር ሂደቶች መዘግየት የሰላም ሁኔታን አደጋ ውስጥ እየከቱት ነው ተብሏል፡፡ሊጠናቀቅ አንድ ዓመት የቀረው የሀገራዊ ምክክር ኮሚሽ እንዲሁም የሽግግር ፍትህ…

የሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን የመሰሉ የንግግር ሂደቶች መዘግየት የሰላም ሁኔታን አደጋ ውስጥ እየከቱት ነው ተብሏል፡፡

ሊጠናቀቅ አንድ ዓመት የቀረው የሀገራዊ ምክክር ኮሚሽ እንዲሁም የሽግግር ፍትህን የመሰሉ ሰነዶች በቶሎ ባለመፅቃቸው አሁንም ሌላ ዙር ግጭት እንዳያመራ ስጋት ሆኗል መባሉም ኢትዮ ኤፍ ኤም ሰምቷል፡፡

የሰሞኑም የሀገሪቱ ሁኔታ በተለይም አንጋፋ የሚባሉ ፖቲከኞች ግድያ እና በአማራ እና ትግራይ ክልል ያገረሸው ውጥረት አሳሳቢ እየሆነ መጥቷል፡፡

በመሆኑም የሀገራዊ ምክክርን የመሰሉ ሁሉን አካታች ውይይቶች መዘግየት ለአሁናዊ የፀጥታ ስጋት ዳርገውናል ሲሉ ከጣብያችን ጋር ቆይታ የነበራቸው የፖለቲካ ፓርቲዎች እና የሲቪክ ማህበረሰብ ድርጅቶች ገልፀዋል፡፡

ከጣብችን ጋር ቆይታ የነበራቸው የኢትዮጵያ ህዝቦች አብዮታዊ ፓርቲ ኢህአፓ ዋና ፀሀፊ የሆኑት ደስታ ጥላሁን የሀገራዊ ምክክር ኮሚሽ፣የሽግግር ፍትህ ሰነዱ በቶሎ ያለመፅደቅ ሁኔታዎች የሰላም ሁኔታውን ጥያቄ ውስጥ እንዲገባ አድርገውታል ብለዋል፡፡

ሌላው ከጣብያችን ጋር ቆይታ የነበራቸው የቪዥን ኢትዮጵያ ኮንግረስ ፎር ዲሞክራሲ ዋና ዳይሬክተር የሆኑት አቶ ታደለ ደረሰ በቶሎ ወደ ንግግሮችና መፍትሄዎች አለመግባት ለሌላ ዙር ግጭት የሚዳርግ በመሆኑ ሊታሰብባቸው ይገባል ብለዋል፡፡

ከዚህ ውጪ በተለያዩ ግዚያት ፖለቲከኞችም ሆነ የሰብዓዊ መብት ተሟጋቾች ሲሰወሩ እንዲሁም ከቀናት በኃላ በተለያዩ ቦታዎች ላይ ታሰረው ይገኛሉ የሚሉት አቶ ታደለ ደርሰህ በወቅቱ ወደ ፍርድ ያለመቅረብ ሁኔታዎችም አሳሳቢ እንዲሁም ህጋዊ አይደሉም ይላሉ፡፡

በቅርቡ ከሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ከመሰሉ የንግግር ሂደቶች እራሴን አገላለው የሚለው የኢትዮጵያ ህዝቦች አብዮታዊ ፖርቲ ኢህአፓ ዋና ፀሀፊ የሆኑት አቶ ደስታ ጥላሁንም በበኩላቸው በአሁን ወቅት በሀገሪቱ ያሉ ሁኔታዎች ለሰላማዊ የፖለቲካ ትግልም ፈታኝ ሆኗል ሲሉ ለጣብያችን ተናግረዋል፡፡
በኢትዮጵያ ሁሉን አቀፍ ውይይት ተካሂዶ አገሪቱ ከምትገኝበት የፖለቲካና ጸጥታ ቀውስ እንድትወጣ ያነጋገርናቸው አካላት ገልፀዋል፡፡

ታጣቂዎች ጭምር የሚሳታፉበት፤ መንገስትም በሀቀኝነት የሚወያይበት አገራዊ ምክክርም ተደርጎ ከወቅታዊ ችግሮች መውጣት የሚቻልበት ሁኔታ መፈጠር ይኖርበታል ተብሏል፡፡

አቤል ደጀኔ
ሚያዚያ 9 ቀን 2016 ዓ.ም

ኤትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የኢትዮጲያዊያን

Source: Link to the Post

Leave a Reply