የሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን 85 በመቶ ከሚሆኑ የፖለቲካ ፓርቲዎች ጋር በጋራ እየሰራን እንገኛለን አለ፡፡

ኮምሽኑ በህጋዊ መንገድ ተመዝግበው እንቅስቃሴ ከሚያደርጉ 85 ከመቶ ፓርቲዎች ጋር በጋራ እየሰራን ነው ማለቱን ኢትዮ ኤፍ ኤም ሰምቷል፡፡

ይሁን እንጂ አሁንም የምክክር ሂደቱ ውስጥ ተሳትፎ የማያደርጉ ፓርቲዎች መኖራቸውን ኮምሸነር መላክ ወልደማርያም ለጣብያችን ተናግረዋል፡፡

የምክክር ሂደት ሊያመልጠን የሚገባ ሂደት አይደለም ስለዚህም ወደዚህ የምክክር ሂደት ሌሎችንም ለማስገባት እየተሰራ ነው ብለዋል፡፡

ጦርነት በፍፁም አመራጭ መሆን የለበትም ያሉት ኮምሸነሩ ችግሮችን በጠረጴዛ ዙሪያ መፍታት የተሻለው አማራጭ ነው ብለዋል፡፡

ይሁን እንጂ ተደጋጋሚ የገለልተኝነት ጥያቄ የሚነሳበት የሀገራዊ ምክክር ኮሚሽኑ በተለይም ለመንግስት ቅርብ ነው ሲሉ አንዳንድ ፓርቲዎች አልተቀበሉትም ፡፡

ይህንንም በተመለከተ ጣቢያችን የኮሚሽኑ ገለልተኛነት ምን ድረስ ሲል ጠይቋል፡፡

አቶ መላክ ሲመልሱም ገለልተኛ ነን ስራችን ገለልተኝነታችንን ያሳያል ሲሉ መልሰዋል።

በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ የሚንቀሳቀሰውና በአካባቢው ምርጫ ያሸነፈው የቁጫ ህዝቦች ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ በኮምሽኑ ተሳታፊ አልተደረኩም ብሎ ለሚያሰማው ተደጋጋሚ ቅሬታ በጠየቅነው ምላሽ፣

ኮሚሽነሩ ስለጉዳዩ የሚያውቁት ነገር አለመኖሩን በመጥቀስ ቅሬታ ያለው ማንኛው አካል ቅሬታ ሰሚ መመሪያ ስላለ ወደዛ በመምጣት ጥያቄውን ማቅረብ ይቻላል ብለዋል፡፡

የሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ሁለት ዓመትን የደፈነ ሲሆን አሁን ላይ አጀንዳ የማሰባሰብ ስራ መጀመሩን በቅርቡ ማስታወቁ አይዘነጋም፡፡

በአቤል ደጀኔ

የካቲት 18 ቀን 2016 ዓ.ም

Facebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Source: Link to the Post

Leave a Reply