የሀገራዊ ምክክር ኮሚሽ በሁለት ሳምንት ውስጥ ክልላዊ እና ከተማ አስተዳደር መድረክ ሊያደረግ መሆኑን አስታወቀ፡፡ኮሚሽኑ የሚፈልገው ያህል አጀንዳዎችም እየመጡለት መሆኑን ኢትዮ ኤፍ ኤም ሰምቷ…

የሀገራዊ ምክክር ኮሚሽ በሁለት ሳምንት ውስጥ ክልላዊ እና ከተማ አስተዳደር መድረክ ሊያደረግ መሆኑን አስታወቀ፡፡


ኮሚሽኑ የሚፈልገው ያህል አጀንዳዎችም እየመጡለት መሆኑን ኢትዮ ኤፍ ኤም ሰምቷል፡፡

ኮሚሽኑ በዌብሳይትም በአካል ከሀገር ውስጥም በውጭ ያሉ አካላት አጀንዳ የሚሆን ሀሳብ እየላኩላቸው መሆኑን የኮሚሽኑ ኮሚሽነር ዶ/ር አምባዬ ኦጋቶ ለጣብያችን ተናግረዋል፡፡

ኮሚሽኑ ከሁለት ሳምንት ገደማ በኃላም የክልሎች እና የከተማ አስተዳደሮች መድረክ ማዘጋጀቱን ኮሚሽነሩ ገልፀዋል፡፡

ይህ መድረክም በቅድሚያ ከአዲስ አበባ የሚጀመር መሆኑን ኮሚሽነር አምባዬ አስረድተዋል፡፡

ይህንን መደረክ ለማከናወን ዝግጀት መጀመሩን የገለፁት ኮሚሽነሩ በዚህ ውስጥ ሶስት ነገር ይጠበቃል ብለዋል፡፡

የመጀመሪያው አጀንዳ ማሰባሰብ ሲሆን ሁለተኛው በአካባቢው ማህበረሰብ የሚፈቱ ጉዳዮችን በዛው መድረክ እየፈቱ የመሄድ ስራ ይሰራል ብለዋል፡፡

ሶስተኛው የዚህ መድረክ ዓላማ ለዋናው የሀገራዊ ምክክር መድረክ የሚሳተፉትን የመለየት ስራ የሚሰራበት ጭምር መሆኑን ሰምተናል፡፡

የሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ከትግራይ እና አማራ ክልል ውጪ 17ሺህ 200 የሚሆኑ ተወካዮች መምረጡንም አስታውቋል፡፡

በአቤል ደጀኔ

ግንቦት 13 ቀን 2016 ዓ.ም

Source: Link to the Post

Leave a Reply