“የሀገሬ ወጣት “አንድ ራስ አንድ ምላስ” ሆነህ ጠላትህን አንበርክክ!” አቶ ወርቁ አይተነውና መልዕክታቸው! አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ… ጥቅምት 13 ቀን 2014 ዓ. ም አ…

“የሀገሬ ወጣት “አንድ ራስ አንድ ምላስ” ሆነህ ጠላትህን አንበርክክ!” አቶ ወርቁ አይተነውና መልዕክታቸው! አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ… ጥቅምት 13 ቀን 2014 ዓ. ም አዲስ አበባ ሸዋ የሀገራችን ደመኛ ጠላት ቅጥረኛው ጁንታ ከአማራ ህዝብ አቅም በላይ ሁኖ አይደለም። ማን መጥቶ እንዲያድንህ ነው እየተለማመጥክ ያለኸው? አባቶቻችን በጣሊያን ጊዜ በነበረው የአየር ድብደባ፣ መርዛማ የኬሚካል ርጭት፣ የብርጭቆ ስብርባሪ በባዶ እግራቸው እየረገጡ በጦርና ጎራዴ ጠላትን እንዳንበረከኩ እረሳነው እንዴ? ታዲያ እኛ የማን ልጆች ሁነን ነው ጠላት በደጃችን መጥቶ እንዲፈነጭብን የፈቀድንለት? የትኛውም ከባድ መሳሪያ ይኑራቸው ብዙ ህዝብም ያሰልፉ በመጡበት አግባብ ህዝባዊ ማዕበል ሁነን በመሬታችን ልናስቀራቸው ይገባል። የባህር ዳር፣አዴት፣ ጭስ አባይ፣ ቋሪትና ደጋ ዳሞት፣ መራይና ዱር ቤቴ፣ ዳንግላ ያለኸው ጀግና በሙሉ በጎንደር ደባርቅና ዳባት፣ የደ/ታቦርና አካባቢው እንደነበረው ወጣት፣ ዛሬ ነገ ሳትል ወሎ ላይ ከሚዋደቀው ጀግና ወንድምህ ጎን በመሆን አብረኸው ልትወድቅ ልትነሳ ያስፈልጋል። በጸረ ወያኔ ትግል ወቅት ከጫፍ እስከ ጫፍ በባዶ እጅህ ተፋልመህ ነጻ የወጣኸው በትብብር መንፈስህ እንደሆነ መለስ ብለህ አስታውስ! ተበትኖ የገባውን ቀጣፊ ጁንታ በወሬው ሳትረበሽ አስፍተህ ዋጠው። ፍኖተ ሰላምና ቡሬ፣ ኮሶበርና ቲሊሊ ያለህ ወጣት በቡሬ በኩል አባይን ሊሻገር ያሰፈሰፈውን የጁንታውን ተላላኪ በንስር አይን ተግተህ ጠብቅ! ሞጣ፣ ግንደ ወይን፣ ደብረ ወርቅ፣ ቢቸና፣ ሸበል በረንታና አዋባል፣ ደጀንና ማርቆስ እንዲሁም ደንበጫ ያለህ ወጣት አባይ ዙሪያውን ጠብቅ! ባሶ ሊበንና ደብረ ኤሊያስ ዙሪያ ያለኸው ጀግና አባይን ለመሻገር ያሰፈሰፈውን፤ ሴትና ህጻናትን በማረድ ጀግና ነኝ የሚለውን የኦነግ ጦር ወረድ ብለህ የጀግና ስራ እንዴት እንደሆነ አሳየው! ቻግኒና ጃዊ ያለኸው ጀግና በመተከል ላለው ወገንህ ደጀን ሁነህ አካባቢህን በንቃት ጠብቅ! በሸዋ ያለህም ወጣት እኩሌታህ በአካባቢህ እህል እያቃጠለ ቅድመ ትንኮሳ የሚያደርግብህን ጠላት ነቅተህ ጠብቅ! ሌላው ግን ወደ ወሎ መትመም ይኖርበታል። እስከመቼ ነው በወያኔ የውርደት ካባን ለብሰን የምኖረው? በባዶ እጅህ የተፋለምከውን ወያኔ እንዴት እናቶችህንና አባቶችህን አፈናቅሎ ለርሃብ ሲዳርግ ዝም ትላለህ? ከነሱ ያነሰ ስብዕና የለህም። አባቶችህም አላስተማሩህም። ስለዚህ በየ አካባቢው ያለው ወጣት የያዘውን ይዞ ወደ ደሴና ኮምቦልቻ ይክተት! የሚማረከውን ታጥቀህ ትመለሳለህ። ባንተ መስዋዕትነት የምትወዳቸው ወገን ዘመዶችህ በክብር ይኖራሉ። ጁንታው ከወሬ በቀር አማራውን ፊት ለፊት ውጊያ እንደማይችለው የጉና ተራራ፣የደባርቅና ዳባት ተራራዎች ምስክር ናቸው። አጠቃላይ የወሎ ወጣት ያልኩህን በፍጹም አትርሳ! አንተ ሸሽተህለት የሚፈነጭ ጁንታ ሊኖር አይገባም። ማዕበል ሁኖ መጥቷል ከሱ በባሰ መልኩ ማዕበል ሁነህ ዋጠው። መንግስት የሚጠበቅበትን ያድርግ። አንተና መሰሎችህ ግን በሰላ መረጃ ጥናት እያደረግህ ጠላትህን በሽምቅ ውጊያ መድረሻ ልታሳጣው ይገባል። ገፍቶ በመጣ ቁጥር አትሽሽለት። በምታውቀው ሸለቆና ተራራ መሽገህ የእግር እሳት ሁንበት። መወቃቀሱን ከድል በኋላ እንደርስበታለን። ድል ለሀገራችን ኢትዮጵያ ወርቁ አይተነው

Source: Link to the Post

Leave a Reply