የሀገር መከላከያ ሰራዊትና የፌደራል ፖሊስ ድምጸ ወያነ ሲጠቀምበት የነበረውን በመቐለ የሚገኘውን ስቱዲዮ ተቆጣጠረ

የሀገር መከላከያ ሰራዊትና የፌደራል ፖሊስ ድምጸ ወያነ ሲጠቀምበት የነበረውን በመቐለ የሚገኘውን ስቱዲዮ ተቆጣጠረ

አዲስ አበባ፣ ህዳር 25፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የሀገር መከላከያ ሰራዊትና የፌደራል ፖሊስ ድምጸ ወያነ ሲጠቀምበት የነበረውን በመቐለ የሚገኘውን ስቱዲዮ መቆጣጠራቸው ተገለፀ።

ከትግራይ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ጽህፈት ቤት እና ሰማእታት ሃውልት አቅራቢያ የሚገኘውን እና ጁንታው ሲጠቀምበት የነበረውን በመቐለ የሚገኘውን ስቱዲዮ የሀገር መከላከያ ሰራዊትና የፌደራል ፖሊስ ተቆጣጥሮታል፡፡

የስቱዲዮው የተለያዩ ክፍሎች እና ቁሳቁሶች በጁንታው ሃይል ጉዳት እንዲደርስባቸውና እንዲወድሙ መደረጋቸውም ታውቋል፡፡

በአሁኑ ሰአትም ስቱዲዮው ሙሉ በሙሉ በመከላከያ እና በፌደራል ፖሊስ ቁጥጥር ስር እንደሚገኝ ተገልጿል፡፡

የድምጸ ወያነ ሬዲዮና ቴሌቪዥን ስቱድዮን ጁንታው ህዝብን የማወናበጃ መረጃዎችን ሲያሰራጭበት እና ለፕሮፖጋንዳው ሲጠቀምበት መቆየቱን ኦቢኤን ዘግቧል፡፡

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤

ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል www.youtube.com/fanatelevision ሰብስክራይብ ያድርጉ

ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ

ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን

 

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

The post የሀገር መከላከያ ሰራዊትና የፌደራል ፖሊስ ድምጸ ወያነ ሲጠቀምበት የነበረውን በመቐለ የሚገኘውን ስቱዲዮ ተቆጣጠረ appeared first on Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C.

Source: Link to the Post

Leave a Reply