
አዲስ አበባ ፣ ህዳር 19 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከተለያዩ ሆስፒታሎች የተውጣጡ ከ60 በላይ የጤና ባለሙያዎች እና ሁለት ድጋፍ ሰጪ አምቡላንሶች ለመከላከያ ሰራዊት ሙያዊ ድጋፍ ለመሰጠት ወደ ስፍራው አቅንተዋል ።
የአዲስ አበባ ከተማ ጤና ቢሮ ኃላፊ ዶክተር ዮሐንስ ጫላን ጨምሮ የከተማ አስተዳደሩ ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች ለህክምና ባለሙያዎች አሸኛኘት አድርገዋል ።
የሀገር ጥሪን በመቀበል ሰራዊቱን በሙያቸው ለማገዝ ዝግጁ መሆናቸውን የገለጹት የጤና ባለሙያዎቹ በዚህም ደስተኛ መሆናቸውን ተናግረዋል ፡፡
በመጀመሪያው ዙር 48 የህክምና ባለሙያዎች የሀገር መከላከያ ሰራዊቱን በማገልገል ላይ እንደሚገኙ ከአዲስ አበባ ፕሬስ ሴክሬታሪያት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።
The post የሀገር መከላከያ ሰራዊትን ለማገዝ ሁለተኛ ዙር የአዲስ አበባ የህክምና ባለሙያዎች ልዑካን ወደ ስፍራው አቀኑ appeared first on Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C.
Source: Link to the Post