የሀገር መከላከያ ሰራዊት ሽሬን ከተቆጣጠረ በኋላ ከተማችን ሰላም ነች – ነዋሪዎች

የሀገር መከላከያ ሰራዊት ሽሬን ከተቆጣጠረ በኋላ ከተማችን ሰላም ነች – ነዋሪዎች

አዲስ አበባ፣ ህዳር 13፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) “የሀገር መከላከያ ሰራዊት ሽሬን ከተቆጣጠረ በኋላ ወደ ሰላማዊ እንቅስቃሴ ተመልሰናል” ሲሉ ያነጋገርናቸው የከተማዋ ነዋሪዎች ገለጹ።
ነዋሪዎቹ የህወሃት ታጣቂ ሃይል እያለ እንቅስቃሴያቸው ተገድቦ በከፍተኛ ችግር ውስጥ እንደነበሩ ገልጸው አሁን ግን ነፃነት እንዳገኙ ተናግረዋል።
በምዕራብ ትግራይ የሕወሃትን ከሃዲ ቡድን በመደምሰስ ከቀናት በፊት የአገር መከላከያ ሰራዊት መቆጣጠሩ ይታወሳል።
ህወሃት “ወራሪ መዝባሪ” እያለ በሃሰት የከተማውን ህዝብ ሲያደናግር በመቆየቱ “መከላከያ ሽሬ ከተማ ገባ ሲባል ፈርተን ነበር” የሚሉት ነዋሪዎቹ ሰራዊቱ ሲገባ ግን በጥሩ ስነ ምግባር ከተማዋን ማረጋገቱን መግለፃቸውን ኢዜአ ዘግቧል።
የሀገር መከላከያ ሰራዊት ፍቅሩን አሳይቶናል፣ አረጋግቶናል፣ ከውጥረትና ፍርሃት እንድንወጣም አድረጎናል ብለዋል።

The post የሀገር መከላከያ ሰራዊት ሽሬን ከተቆጣጠረ በኋላ ከተማችን ሰላም ነች – ነዋሪዎች appeared first on Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C.

Source: Link to the Post

Leave a Reply