ኢትዮጵያ በርካታ የቱሪስት መደረሻ ስፍራዎች ቢኖሯትም ከዘርፉ የምታገኘው ገቢ ዝቅተኛ ነው፡፡ኢትዮጵያ የቱሪስት ገቢያቸው ካደጉ ሀገራት ተርታ እንትመደብ ካደረጓት ምክንያቶች መካከል አንዱ ለአለማቀፍ ማህበረሰቡ በቂ ትውውቅ አለመደረጉ እና የመገናኛ ብዙሃንም ለዘርፉ የሰጡት አናሳ ትኩረት መሆኑን ቢሮው ገልጿል፡፡
ሌሎች ሀገራት በዓለም አቀፍ መገናኛ ብዙሃን ቱሪዝማቸውን ያስተዋወቃሉ ያሉት የቢሮ ምክትል ሃላፊ አቶ ሁንዴ ከበደ ናቸው፡፡ኢትዮጵያ በቂ የገንዘብ አቅምን ባለማካበቷ በዓለማቀፍ ደረጃ ራሷን ማስተዋወቅ አለመቻሏን አቶ ሁንዴ ለአሀዱ ገልፀዋል፡፡በዚህ ረገድም የመገናኛ ብዙሃን በቱሪዝም እድገት ትልቅ ድርሻ አላቸው ያሉት የቢሮው ምክትል ሃላፊ ቱሪዝሙን ለማሳደግ በሚገባ ማስተዋወቅ ያስፈልጋል ብለዋል፡፡
አዘጋጅ ወንድማገኝ ሃይሉ
Source: Link to the Post