የሀጫሉ ሁንዴሳ ግድያ የፍርድ ሂደት

ከሀጫሉ ሁንዴሳ ግድያ ጋር በተያያዘ ክስ በቀረበባት ላምሮት ከማል ላይ ፍርድ ለመስጠት ተላዋጭ ቀጠሮ ተሰጠ፡፡

አርቲስት ሀጫሉ እንዲገደል ቦታ አመቻችታለች ተብላ በሽበር ወንጀል የተከሰሰችው ላምሮት ከማል ፍርድ ቤቱ በወንጀለኛ መቅጫ ሥነ-ሥርዓት ህግ አንቀጽ 113/2 መሰረት ተከሳሽ የተከሰሰችበትን የሽብር ወንጀል አንቀጽ በማሻሻል አደጋ ላይ የሚገኝ ሰውን ባለመርዳት የወንጀል የወንጀል ህግ አንቀጽ 575 ስር እንድትከላከል ብይን ተሰጥቶ እንደነበር ይታወሳል፡፡

በዚህም መሰረት ፍርድ ቤቱም ኅዳር 23/2014 ዓ.ም ባስቻለው ችሎት ተከሳሿ በችሎት ቀርባ መከላከያ ማስረጃ የለኝም በማለቷ የመከላከል መብቷ ታልፎ ፍርድ ለመስጠት ለህዳር 29/2014 ዓ.ም ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቷል ሲል ፍትሕ ሚኒስቴር በፌስቡክ ገፁ ላይ አስፍሯል፡፡

ቀን 23/03/2014

አሐዱ ቴሌቪዥን

Source: Link to the Post

Leave a Reply