የሁለተኛው ዙር የዳሸን ከፍታ የስራ ፈጠራ ውድድር አሸናፊዎች ተሸለሙ።ለአሸናፊነት ለደረሱ ተወዳዳሪዎች በአጠቃላይ ሁለት ሚሊየን ሀምሳ ሺህ ብር ተበርክቷል።ዳሽን ባንክ ባዘጋጀው ሁለተኛ ዙ…

https://cdn4.cdn-telegram.org/file/HHHXXnufiLU_Vey2aLxJQToEM3eUtaODgyPTNOISpaMoAKNDWkwK8i-s5OnOkKPVXnEIKDMQ8FK10UngKdZ8SYFy5jqYyN4xiUgHI0Ek1SP5ly5gygKSumCnVk2U2V56zhOHkQ09luOZDZUB2ALWCm9NWQst0MYvfO3X_kEIjQ8KjfJFCzpZiMDjrAGzr6SI5GM5perhD5yzX6S49BbY0wzccO6d4JqOrbPPAPfAVxVAAW6rxmg1QEU3r_6ZVnHPX3znRJue134n-sJ-OLsEG9V4TM7sML6UTYvRl7yacB-TL9aOY9xxbNefOY7uAHr6Xs86Dx0yWyzi2GAU4lzxmA.jpg

የሁለተኛው ዙር የዳሸን ከፍታ የስራ ፈጠራ ውድድር አሸናፊዎች ተሸለሙ።

ለአሸናፊነት ለደረሱ ተወዳዳሪዎች በአጠቃላይ ሁለት ሚሊየን ሀምሳ ሺህ ብር ተበርክቷል።
ዳሽን ባንክ ባዘጋጀው ሁለተኛ ዙር የስራ ፈጠራ ውድድር ላይ ከተሳተፍ ከ 6 ሺ በላይ ተወዳዳሪዎች ከ 1- 10 የወጡ ተወዳዳሪዎች የገንዘብ ሽልማት ተበርክቶላቸዋል።

አንደኛ ለወጣው የስራ ፈጠራ አሸናፊ የ 5 መቶ ሺህ ብር ሽልማት ተበርክቷል።
ከ 6- 10ኛ ለወጡ አሸናፊዎችም ለእያንዳንዳቸው የ 1 መቶ ሺ ብር የገንዘብ ሽልማት ተበርክቷል።

በፈጠራ ውድድር አሸናፊዎች ሽልማት መረሃ ግብር ላይ የተገኙት የስራ እና ክህሎት ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ንጉሱ ጥላሁን ሃሳብ ያላቸው ወጣቶችን ለይቶ እና አሰልጥኖ ለዚህ ማብቃት ብቻውን አሸናፊነት ነው ብለዋል።

ሚንስቴር መስሪያ ቤቱ እንደዚህ ያሉ የስራ ፈጣሪዎችን እንደሚያበረታታም ተናግረዋል።

የዳሽን ባንክ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ አስፋው ዓለሙ በበኩላቸው ባንኩ ማህበራዊ ሃላፊነቱን ለመወጣት ከነደፋቸው ትልልቅ መርሃ ግብሮች አንዱ ይህ የስራ ፈጠራ ውድድር መሆኑን ጠቁመው በመርሃ ግብሩ በተለያዩ የአገሪቱ ክፍሎች ስድስት ሺህ ተወዳዳሪዎችን ማሳተፍና ተጠቃሚ ማድረግ መቻሉን አመልክተዋል፡፡

ባንኩ ከአሸናፊዎች ጋር ለወደፊት አብሯቸው እንደሚሰራና ድጋፍ እንደሚያደርግላቸውም ጭምር ቃል ገብተዋል፡፡
ሶስተኛው ዙር የዳሽን ከፍታ ውድድር በቅርቡ ይጀመራል ተብሏል፡፡

በየውልሰው ገዝሙ

ህዳር 25 ቀን 2016 ዓ.ም

Source: Link to the Post

Leave a Reply