የሁለቱ ምክር ቤቶች የጋራ የመክፈቻ ስነ-ስርዓት ነገ ይካሄዳል።የ6ኛው የኢፌዴሪ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤትና የፌዴሬሽን ምክር ቤት 2ኛ ዓመት የስራ ዘመን መክፈቻ ስነ-ስርዓት ነገ መስከረም…

https://cdn4.telegram-cdn.org/file/M1mE8TKhNm4cDz7sXiRFV8XIbG4lZlAHxeOIPcuyc1nb7Lq9jdAV7KuzUgFxUcq4c2hpBLoZU8-7_Xv-EY-ZuBh6tWN0pscayqEHiFUJFCc9vjobGpww3U07KzZY-7aw_iG6mwZYKZwlOcYFjOpFeWDaDNF9IIWjNx9Jyef94UWNq-9oUCDI6alOL_2JwyGrX6xdhhF5tsgcXN1Ulix_9BqC1fd7QKuya6vFQKLuBATKdtftgIsbpdcOPD0dXKhCmAsvbvE-pzcgM0gKrjRow5KycgMiZqCHmnwLeOL6D-LuOScVGCYlPyJOeCDakWV2FDZthogpi0NhFBjv-arHsw.jpg

የሁለቱ ምክር ቤቶች የጋራ የመክፈቻ ስነ-ስርዓት ነገ ይካሄዳል።

የ6ኛው የኢፌዴሪ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤትና የፌዴሬሽን ምክር ቤት 2ኛ ዓመት የስራ ዘመን መክፈቻ ስነ-ስርዓት ነገ መስከረም 30 ቀን 2015 ዓ.ም ይካሄዳል።

በኢፌዴሪ ሕገ-መንግስት አንቀፅ 58 ንዑስ አንቀፅ 2 መሰረት የኢፌዴሪ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የአንድ ዓመት የስራ ጊዜ ከመስከረም ወር የመጨረሻ ሳምንት ሰኞ ጀምሮ እስከ ሰኔ 30 ቀን ድረስ መሆኑን ይደነግጋል፡፡

ሁለቱ ምክር ቤቶች ባለፈው 2014 ዓ.ም የ1ኛ ዓመት የስራ ዘመናቸውን አጠናቀው እነሆ በ2015 ዓ.ም የ2ኛ ዓመት የስራ የዘመናቸው የሚይዙ ይሆናል፡፡

ስለሆነም 6ኛው የኢፌዴሪ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤትና የፌዴሬሽን ምክር ቤት 2ኛ ዓመት የስራ ዘመን የጋራ መክፈቻ ሥነ-ስርዓት ሰኞ መስከረም 30 ቀን 2015 ዓ.ም የሪፐብሊኩ ፕሬዚዳንት በሚገኙበት ከቀኑ 8፡30 ጀምሮ ይካሄዳል፡፡

በመክፈቻ ስነ-ስርዓቱ ላይ የኢፌዴሪ ፕሬዚዳንት ክብርት ሳህለወርቅ ዘውዴ የመንግስት ዕቅድን በሚመለከት ለሁለቱ ምክር ቤቶች ንግግር እንደሚያሰሙ ይጠበቃል።

በአዲስ አበባ የሚገኙ የተለያዩ ሀገራት አምባሳደሮች፣ የዓለም አቀፍ ተቋማት ተጠሪዎች፣ የሃይማኖት አባቶችና ሌሎች ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች በመክፈቻ ስነ-ስርዓቱ ላይ የሚገኙ ሲሆን የመክፈቻ ስነ-ስርዓቱም ሂደት በቀጥታ ስርጭት የሚተላለፍ ይሆናል፡፡

ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የኢትዮጵያዊያን

መስከረም 29 ቀን 2015 ዓ.ም

Source: Link to the Post

Leave a Reply