
የሁለቱ ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት ክቡር አስክሬን ከመንበረ ፓትርያርክ ቅድስተ ቅዱሳን ማርያም ገዳም ወደ መንበረ ጸባዖት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል በክብር ደርሷል። #Ethiopia |™መጋቢት ፲፮ ቀን ፳፻፲፭ ዓ.ም የብፁዕ አቡነ ባስልዮስ እና የብፁዕ ዶ/ር አቡነ አረጋዊ ክቡር አስከሬን በክብር ካረፈበት በብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት፣በሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያን፣ በቤተሰቦቻቸው እና በምእመናን ታጅቦ ወደ መንበረ ፓትርያርክ ቅድስተ ቅዱሳን ማርያም ገዳም በክብር የገባ ሲሆን ፤ሌሊት የማህሌትና የሰዓታት ቁመት ሲከወን አድሯል። መጋቢት ፲፮ ቀን በዛሬው ዕለትም ከጠዋቱ 2:30 በክብር ካረፈበት ከመንበረ ፓትርያርክ ቅድስተ ቅዱሳን ማርያም ገዳም በብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት እና በሊቃውንተ ቤተክርስቲያን በሰንበት ት/ቤት ዘማርያን እንዲሁም በወዳጅ ዘመዶቻቸ…ው ክቡር አስክሬናቸው ታጅቦ ስርዓተ ቀብሩ ወደሚከወንበት ወደ መንበረ ጸባዖት ቅድስት ሥላሴ ደርሷል። በመንበረ ፀባዖት ቅድስት ሥላሴም በብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ፓትርያርክ እንዲሁም በብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት ሥርዓተ ጸሎት ሥርዓተ ቀብራቸው እንደሚፈፀም ታውቋል። “ውድ የአሻራ ሚዲያ ቤተሰቦች የአሻራ ሚዲያ ቻናልን ላይክና ሰብስክራይብ በማድረግ ድጋፋችሁን ታሳዩን ዘንድ በአክብሮት እንጠይቃለን።” ለፈጣንና አዳዲስ መረጃዎች አሻራ ሚዲያ የአይበገሬዎቹ ልሳን:- // Youtube:- https://www.youtube.com/channel/UCPmgFzP2ZPmdGjHxXjigJaw // Facebook:- https://www.facebook.com/asharamedia24 // ቴሌግራም:- https://t.me/asharamedia24
Source: Link to the Post