You are currently viewing የሃያሉ አማራ ትግል ተጠናክሮ ይቀጥላል! ~~~~~~ በአሸናፊ ገናን ~~~~~~~ አሻራ ሚዲያ … ሰሜን አሜሪካ  አማራነት /ሞት ሲል የነበረውን ተልከስካሺ ድርጅትም በአማራ ወርድ እና ቁመ…

የሃያሉ አማራ ትግል ተጠናክሮ ይቀጥላል! ~~~~~~ በአሸናፊ ገናን ~~~~~~~ አሻራ ሚዲያ … ሰሜን አሜሪካ አማራነት /ሞት ሲል የነበረውን ተልከስካሺ ድርጅትም በአማራ ወርድ እና ቁመ…

የሃያሉ አማራ ትግል ተጠናክሮ ይቀጥላል! ~~~~~~ በአሸናፊ ገናን ~~~~~~~ አሻራ ሚዲያ … ሰሜን አሜሪካ አማራነት /ሞት ሲል የነበረውን ተልከስካሺ ድርጅትም በአማራ ወርድ እና ቁመት ልክ ሆኖ እንድሰፋ የምንታገል ይሆናል። አማራነት በደም እና በአጥንት ተገንብቶ ነፃ ሃገር እንድሆንም የምንሰራ ይሆናል። ሃያሉ አማራ ለእኩልነት፣ለፍትህ እና ለድሞክራሲ እንድታገልም የምናደርገው ይሆናል። በአሁኑ የፓለቲካ ሁኔታ አማራው እንደ ሁለተኛ ዜጋ እንኳ ሆኖ መኖር የማይችልበት ደረጃ ላይ ደርሷል። አማራውን በሁሉም አቅጣጫ የሚያሳድድ ስርዓት እና ስሪት ተቋቁሞ የአማራው ህልውና የብሄራዊ አደጋ ስጋትን ፈጥሯል። ስለሆነም በሁሉም አቅጣጫ የሚታዩ ተግዳሮቶች መነሻው የፀረ አማራ ሃይሎች ጥምረት የፈጠረው እንቅስቃሴ መሆኑ ግልፅ ነው። ህዝባችንን በኢኮኖሚ፣በማህበራዊ ፍትህ እና በመልካም አስተዳደር ችግር ውስጥ መኖሩ እየታወቀ በመንግስት በኩል እየተደረገ ያለው ከመጠን ያለፈ ውንብድና ሃላፊነት የጎደላቸው ሃይሎች መንበረ ስልጣኑን ስለተቆጣጠሩት ነው። በሰሞነኛ የአማራ ፓለቲካ ውስጥ ህግ ማስከበር በሚል ሰበብ ህዝባችን እና አማራዊ አስተሳሰቦችን ለመስበር የተሄደበት ሩቅ መሆኑን አይተናል። ነገር ግን #አማራነት በወንበደዎች እና በተስፈኞች የሚሰበር የሸክላ ዕቃ አይደለም። ወደረኞቻችን ያላወቁት ነገር ቢኖር #አማራነት ስጋ እና ደም ሆኖ መወለዱ ነው። ከዚህ አኳያ አማራነት ማለት ብአደናዊነት /አብንነት አይደለም። አማራነት ደም ነው። የቅርብ ጊዜ ብሔርተኞች እና በወያኒያዊ ትርክት ፀንፈኝነት የሚሉት አስተሳሰብ በራሱ ሰው ሆኖ ተወልዶ አድጎ ኢትዩጲያን እየበላ ያለን ስርዓት በቀላሉ የምንመለከተው አይደለም። በግልፅ ቋንቋ በዘር መደራጀትን የሚፈቅድ ህገ መንግስት ያላት ሃገር በሌላ መልኩ ደግሞ አንቀፅ 39 የብሔር ብሔረሰቦች መብት እሰከ መገንጠል የሚል አርቲክል ያላት ሃገር በምንም መመዘኛ የአማራ ብሔርተኝነትንና አደረጃጀትን መክሰስም መውቀስም አይቻልም። ስለሆነም አማራ እንደ ህዝብ መወቀስ ካለበትም በጊዜ አለመደራጀቱ ብቻ ነው።ከዚህ ውጭ በብሔር ኮታ ስልጣን፣በጀት እና የሰው ሃይል የምትመድብ ሃገር የአማራን ተቋማት ለመርገም እና በስጋት ለማየት መሞከር ተቀባይነት የለውም። በአሁናዊ የኢ/ያ ፓለቲካ የአማራ ህዝብ ችግር #ከፓርቲ በላይ መሆኑ ይታወቃል። ነገር ግን አማራውን ለመናኛ ጥቅም የተጠቀሙ የፓለቲካ ሀይሎች እና ሲቪክ ማህበራት ጭምር የአማራ ህዝብ ወንጀለኞች ናቸው። በአማራ ህዝብ የተደራጁ እና ጥቅሙን፣ህልውናውንና ክብሩን አሳልፈው የሸጡ ሁሉ በታሪክ የምንፋረዳቸው ናቸው። ከዚህ አኳያ አብን/የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ ፣ የአማራ ባንክ እና አስራት ሚድያ በአድሱ ትውልድ የተመሰረቱ የአማራ ህዝብ አንጡራ ሃብቶች የነበሩ ናቸው። ነገር ግን ከግል ክብረኝነት፣ከረስ ወዳድነት እና በአሉባልታ በሚመነጭ ሁኔታ ብዙ ተቋሞች በውጥንነት ተጀምረው በብአደናዊያንና መሰሎቻቸው ከስመዋል። በቅርብ ጊዜ ደግሞ አስራት ሚድያ መፍረሱ ይታወሳል።አሁን ደግሞ አብንን ለማፍረስ እየተሰራ ያለውን አሻጥር አንዱ የፓለቲካ አካል ነው። በሌላ መልኩ የአማራ ትግል ተጠናክሮ መቀጠል አለበት የምንለው በሃገር መንግስቱ የሚኖረንን ሚና እኩል ሃላፊነት እንድኖረንም ጭምር ነው። ህዝባችን የተለየ የፓለቲካ እና ማህበራዊ ጥቃት እንዳይደርስበትም ዘረፈ ብዙ ትግል ማድረግ ያስፈልጋል። የአማራ ህዝብ ማህበራዊ ወረቱን ኢ/ያዊነት ላይ በማድረጉ ያገኛቸውንና ጥቅሞች እና ዕድሎች ሁሉ ገምገሞ እንድጨርስ የ 31 ዓመታት የፓለቲካ ጉዞውን ተመልክተናል።በዚህ ሂደት ውስጥም ያተረፋቸው ትርፎች ማህበራዊ ህላዌየውን እና ማህበራዊ መሰረቱ እንድነጋ ምክንያት መሆኑ በሚገባ መረዳት ችሏል። በህዝባችን ላይ የተጫኑ ትርክቶች መዳረሻቸውን ሁሉ አማራን ዕረፍት አልባ ከማድረግም በላይ ህልውናውን እንድያጣ ምክንያት ሆነዋል። የሃያሉ አማራን አስፈሪነት፣አንድነት እና ተጠናክሮ የመቀጠል ህልም እንደ ወደረኞቻችንና እና እንደ ብአደናውያን ሳይሆን እንደ ጠንካራው ህዝባችን ጥንካሬ እና ድክመት የሚወሰን ይሆናል። ስለሆነም የሃያሉ አማራ መደራጀት ለሃገረ መንግስቱ በእጅጉ ጠቃሚ መሆኑንም እንኳን ነባሩ የኢትዮጲያ ህዝብ ቀርቶ ምዕራባውያንና ተላላኪወቻቸውም ያውቁታል። ኢትዮጲያ እንደ ሃገር ለመቀጠል በአብሮነት እና በወንድማማችነት ላይ የተመሰረተ ህግ እና ስርዓትን መትከል ይገባታል። ይህ በሌለበት ሁናቴ #የአማራ ብሔርተኝነት ያስፈራኛል ማለት ሃላፊነት የጎደለው ተግባር መሆኑም ይታወቅ!! የአማራ ብሔርተኝነትንና የሃያሉ አማራ ጥንካሬ የሚያስፈራቸው ሃይሎች ከወደረኞቻችንም በላይ በውስጣችን የተሰገሰጉ ድንክ ፓለቲከኛ ነን ባዮችም አሉ።በተለይም ከቅርብ ጊዜ ወድህ የአማራ ብሔርተኛ ነን በማለት ክልሉን ለማፍረስ እየሰራ ያለውን #የደመቀ መኮነን እስኳድ በቀላሉ የምንመለከተው አይደለም። የአማራ ህዝብ የውስጥ አንድነቱ #ሃይሉ እና ጌጡ ነው።ጥቅመኞች በመከካላችን ውስጥ ሆነው ለአነስተኛ ጥቅም ብለው ታላቁን አማራ ለማሳነስ የሚንደፋደፉ ሁሉ አደብ እንድገዙም እንመክራለን። ትላንት በአማራነት ሲምሉ ሲገዘቱ የነበሩ ህዳጣን ሁሉ ዛሬ ላይ አካባቢን እየጠቀሱ የሚወቅሱትን ነገር አሳፋሪም አሳዛኝም ነው።የአማራ ህዝብ ደመኛ ጠላቶች በስሙ እየተደራጁ ግብራቸው እና ስራቸው ደግሞ ከጠላትም በላይ የሆኑ ሁሉ የታሪክ ተጠያቂ ናቸው። ከዚህ አንፃር ትግላችን እንዳይመለስ ሆኖ ይስራ ዘንድ ብሄርተኝነቱ ተፀንሶ ተወልዷል። አማራነት /ሞት የሚለውን የደም ነጋደ ሁሉ በተግባር ሰርተን የምናሳየው ብዙ ዕድሎች እና አጋጣሚዎች አሉ። ከዚህ አኳያ አማራነት ልክ እንደ #አማራ ባንክ ያሉ በመሬት ላይ ተሰርተው ለብዙሃኑ የስራ፣የህይዎት እና የአንድነት ተስፋ ሆነው በትውልድ ላይ ፀንተው እንድቁሙ እንሰራለን። የሃያሉ አማራ ሁለንተናዊ ትግል ተጠናክሮ ይቀጥላል።እናሸንፋለን!! ምንጭ:- አሸናፊ ገናን

Source: Link to the Post

Leave a Reply