የሃገር ክህደት ወንጀል በፈፀሙ የጁንታው ሕወሓት ቡድን አባላት ላይ የፍርድ ቤት የመያዣ ትዕዛዝ ወጣባቸው

የሃገር ክህደት ወንጀል በፈፀሙ የጁንታው ሕወሓት ቡድን አባላት ላይ የፍርድ ቤት የመያዣ ትዕዛዝ ወጣባቸው

አዲስ አበባ፣ህዳር 3 ፣2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የሃገር ክህደት ወንጀል በፈፀሙ የጁንታው ሕወሓት ቡድን አባላት ላይ የፍርድ ቤት የመያዣ ትዕዛዝ እንደወጣባቸው የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን አስታወቀ።

የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን ለመገናኛ ብዙሃን በላከው መግላጫ እንደገለጸው÷ የጁንታው የሕወሓት ወንበዴ ቡድንን በበላይነት በመምራት በትግራይ ክልል በሚገኘው በሀገር መከላከያ ሰራዊት ሰሜን ዕዝ ላይ ጥቃት በመፈፀም የሃገር ክህደት ወንጀል የፈጸሙት የጁንታው የጥፋት ቡድን አባላትን አድኖ ለህግ ለማቅረብ የፍርድ ቤት ትዕዛዝ ወጥቷባቸዋል፡፡

የጥፋት ቡድኑ አባላት ከኦነግ ሸኔ እና ከሌሎች ፀረ-ሰላም ሃይሎች ጋር በመቀናጀትም ከተለያዩ ክልሎች ሃገርን የማፍረስ ተልዕኮ ያላቸውን ኃይሎች በመመልመል ትግራይ ክልል ድረስ በመውሰድ ለእኩይ ተልዕኮቸው ስኬት የተለያዩ ስልጠናዎችን በመስጠት እንዲሁም የገንዘብና የቁሳቁስ ድጋፎችን በማድረግ በተለያዩ የሃገሪቱ አካባቢዎች ብሄርን ከብሄር በማጋጨት እና በሃይማኖት ሽፋን ሁከትና ብጥብጥ እንዲፈጠር በማድረግ በርካታ ንፅሁን ዜጎች እንዲገደሉ፣ በአካልና በንብረት ላይም ከባድ ጉዳት እንዲደርስ ማድረጋቸውን የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን በላከው መግለጫ አመልክቷል፡፡

እነዚህ የሀገር ህልውናን አደጋ ላይ በመጣል እንዲሁም ህገ-መንግስቱንና ህገ-መንግስታዊ ስርዓቱን በሀይል በመናድ ወንጀል የሚፈለጉትና የፍርድ ቤት የመያዣ ትዕዛዝ የወጣባቸው፡-

1. ዶክተር ደብረፅዮን ገብረሚካኤል

2. ጌታቸው ረዳ

3. ፈትለወርቅ ገብረእግዚአብሄር

4. አስመላሽ ወልደስላሴ

5. ዶክተር አብርሃም ተከስተ

6. ኬሪያ ኢብራሂም

7. ረዳይ አለፎም

8. አማኑኤል አሰፋ

9. ዶክተር አትንኩት መዝገቡ

10. ኪሮስ ሀጎስ

11. ያለም ፀጋ

12. ሰብለ ካህሳይ

13. ጌታቸው አሰፋ

14. ዳንኤል አሰፋ

15. ኢሳያስ ታደሰ

16.ዶክተር አክሊሉ ሀይለሚካኤል

17. አለም ገብረዋህድ

18. ተክላይ ገብረመድህን

19. ዶክተር እያሱ በርሄ

20. ዶክተር ረዳይ በርሄ

21. ዶክተር ኪዳን ማርያም በርሄ

22. ነጋ አሰፋ

23. ሺሻይ መረሳ

24. ዶክተር ገብረህይወት ገብረእግዚአብሄር

25. አፅብሃ አረጋዊ

26. ዶክተር ኢንጅነር ሰለሞን ኪዳኔ

27. ሀዱሽ ዘነበ

28. በርሄ ገብረእየሱስ

29. ይትባረክ አምሃ

30. ዶክተር ገብረመስቀል ካህሳይ

31. ዶክተር ፍስሃ ሀ/ፂዮን

32. ርስቀ አለማየሁ

33. ዶክተር አዲስ አለም ቤሌማ

34. ዘነበች ፍስሃ

35. ፍሬወይኒ ገብረእግዚአብሄር

36. አቶ ስዩም መስፍን

37. አቶ አባይ ፀሐዬ

38. እያሱ ተስፋይ

39. ለምለም ሀድጎ

40. ፕሮፌሰር ክንድያ ገብረህይወት

41. ሀብቱ ኪሮስ

42. በየነ ምክሩ

43. ካሳዬ ገብረህይወት

44. ሩፋኤል ሽፈራ

45. ሊያ ካሳ

46. ተወልደ ገብረፃዲቅ

47. ሙሉ ገብረእግዚአብሄር

48. ኪሮስ ጉዑሽ

49. ዶክተር አማኑኤል ሀይሌ

50. ደሳለኝ ተፈራ

51. ኢንጅነር አርአያ ብርሀኔ

52. አልማዝ ገብረፃድቅ

53. ሰለሞን መአሾ

54. ተኪኡ ማዕሾ

55. ገነት አረፈ

56.ብርክቲ ገብረመድህን

57. ዶክተር ሀጎስ ገዳፋይ

58. ዘራይ አስጎዶም

59. አሰፋ በላይ

60. አቶ ሸዋንግዘው ገዛኸኝ

61. አፅብሃ ግደይ

62. አቶ ስብሀት ነጋ

63. አቶ ሴኮቱሬ ጌታቸው

64. በሪሁን ተክለብርሃን የፌደራል ከፍተኛ ፍርድቤት ዳኛ የነበሩ ናቸው፡፡

ከላይ ስማቸው የተዘረዘረው የወንበዴው የጁንታው ሕወሓት የጥፋት ቡድን አባላት የሃገር ክህደት ወንጀል ከመፈጸማቸውም በተጨማሪ በከፍተኛ የሃገር ሃብት ምዝበራና ዘረፋ እንዲሁም በሰብአዊ መብት ጥሰት ወንጀልም ጭምር የሚፈለጉ መሆናቸውን ፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን በመግለጫው አስታውቋል፡፡

በተመሳሳይም ከጁንታው ሕወሓት ቡድን አባላት ጋር እየተገናኙ የሀገር ክህደት ወንጀል በፈፀሙና ሃገር በማፍረስ ሴራ በተሳተፉ የሀገር መከላከያ ሰራዊት እና የፖሊስ አመራሮች ላይም የፍርድ ቤት የመያዣ ትዕዛዝ እንደወጣባቸውም ነው የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን በመግለጫው ያስታወቀው፡፡

ተጠርጣሪዎቹ መንግስት እና ሕዝብ የጣለባቸውን ሃገራዊ ኃላፊነትና ህገመንግስታዊ ግዴትታን ወደጎን በመተው መቀመጫውን ትግራይ ክልል ካደረገው ከወንበዴው የህወሓት የጁንታው ቡድን አባላት ተልዕኮ በመቀበል በሰሜን ዕዝ ሰራዊት አባላት ውስጥ ሴሎችን በማደራጀት ከማዕከል የነበረው ግንኙነት እንዲቋረጥና ጥቅምት24 ቀን 2013 ዓ.ም ጥቃት እንዲፈጸም በማድረግ የሞት፣የአካል ጉዳት እና የጦር መሳሪያ ዝርፊያ እንዲፈፀም ማድረጋቸውን የኮሚሽኑ መግለጫ ያመለክታል፡፡

ባለፉት 21 አመታት በምሽግ አብረው ሲኖሩ የነበሩ ጓዶቻቸውን የጁንታው ቡድን እኩይ አላማ ማስፈጸሚያ በማድረግ ሃገር በማፍረስ ተልዕኮው በመምራትና በመሳተፍ የሚፈለጉት ከፍተኛ ወታደራዊ መኮንኖችና የፖሊስ አባላት፡-

1.ሌተናል ጀኔራል ታደሰ ወረደ ተስፋዬ (ውድወርደ)

2.ሜጀር ጄኔራል ዮሐንስ ወልደጎርጊስ ተስፋይ (መዲድ)፣

3.ሜጀር ጄኔራል ብርሃነ ነጋሽ በየነ (ውድመድህን)፣

4.ብርጋዴር ጄኔራል ሀይለስላሴ ግርማይ ገብረሚካኤል

5.ብርጋዴር ጄኔራል ምግበ ሃይለ ወልደአረጋይ (አባበርሃ፣)

6.ሜጀር ጄኔራል ኢብራሂም አብዱልጀሊል መሀመድዙን

7.ብርጋዴር ጄኔራል ገብረኪዳን ገብረማርያም የእብዮ

8.ሜጀር ጄኔራል ገብረ ገ/አድሃና ወ/ዘጉ (ገብረዲላ)

9.ሜጀር ጄኔራል ገብረ መስቀል ገብረዮሀንስ /አስቴር/

10.ብርጋዴር ጄኔራል አብርሃ ተስፋይ በርሄ /ድንኩል/

11.ብርጋዴር ጄኔራል ፍስሃ በየነ (ወርቅአይኑ)

12.ሜጀር ጄኔራል ህንፃ ወ/ጎርጊስ ዮሐንስ

13.ብርጋዴር ጄኔራል አለፎም አለሙ ወ/ማርያም /ቸንቶ/

14.ብርጋዴር ጄኔራል ገብረ መስቀል ገ/እግዝያብሄር (ጠቀም)

15.ብርጋዴር ጄኔራል ተ/ብርሃን ወ/አረጋዊ

16.ሜጀር ጄኔራል አታክልቲ በርሄ ገ/ማርያም

17.ኮሚሽነር መኮንን ካህሳይ ገ/መስቀል (ፅንቡላ) የትግራይ ክልል ፖሊስ ኮሚሽነር

18.ምክትል ኮሚሽነር መንግስቴ አረጋዊ የትግራይ ክልል ፖሊስ ም/ኮሚሽነር

19.ኮ/ር ጌታቸው ኪሮስ የትግራይ ፖሊስ አመራር የነበረ

20.ም/ኮሚሽነር ግርማይ ከበደ (ማንጁስ/ የፌደራል ፖሊስ ወንጀል መከላከል ዘርፍ ሃላፊ የነበረ

21.ም/ኮሚሽነር ተክላይ ፀሃዬ የፌደራል ፖሊስ ወንጀል መከላከል ዘርፍ ም/ሃላፊ የነበረ

22.ኮ/ር ንጉስ ወ/ገብርኤል የትግራይ ልዩ ሃይል ፖሊስ ሃላፊ፣

23.ኮ/ር ገ/ስላሴ ታፈረ የፌደራል ፖሊስ ወንጀል መከላከል አመራር የነበረ

24.ኮ/ር ፍስሃ ተ/ማርያም (ወዲአርባ) የፌደራል ፖሊስ ወንጀል መከላከል አመራር የነበረ

25.ኮ/ር ተስፋዬ ገ/ኪዳን (ተስፋዬ ባንዳ) የፌደራል ፖሊስ ወንጀል መከላከል አመራር የነበረ 26.ሜ/ጀነራል ገ/መድህን ፍቃዱ ሃይሉ (ውድነጮ) በቁጥጥር ስር የዋሉ

27.ሜ/ጀነራል ይርዳው ገ/መድህን ገ/ፃድቅ(አስቴር)በቁጥጥር ስር የዋሉ

28.ብ/ጀነራል ገ/ህይወት ሲስኖስ ገብሩ በቁጥጥር ስር የዋሉ

29.ብ/ጀነራል ኢንሶ እጃጆ እራሾ በቁጥጥር ስር የዋሉ

30.ብ/ጀነራል ፍስሃ ገ/ስላሴ እንሁን በቁጥጥር ስር የዋሉ

31.ኮ/ል ደሳለኝ አበበ ተስፋዬ በቁጥጥር ስር የዋሉ

32.ኮ/ል እያሱ ነጋሽ ተሰማ በቁጥጥር ስር የዋሉ

መላው የሃገራችን ህዝቦች፤ የሀገር መከላከያ ሰራዊት፤ የአገራችን የፖሊስ ሰራዊትና የደህንነት ተቋማት እነዚህን የጁንታውን የሕወሓት የጥፋት ቡድን ተፈላጊዎች አድኖ ለህግ ለማቅረብ እየተደረገ ባለው ጥረት በያላችሁበት የድርሻችሁን እንድትወጡ ኮሚሽኑ ጥሪ እያቀረብ፤ በተለይም ደግሞ የትግራይ ህዝብ፤የክልሉ ልዩ ሀይል አባላትና ሚሊሻዎች፤ የጁንታው የሕወሓት ወንበዴ ቡድን ልጆቻቸውንና ቤሰተቦቻቸውን በወጭ አገራት በድሎትና በቅንጦት እያኖሩ የድሃውን የትግራይ ህዝብ ልጅ ለእኩይ አላማቸው መፈጸሚያ ከእሳት እየማገዱ በመሆኑ ይህንን ተገንዘበን ይሄንን የጥፋት ቡድን አድናችሁ በመያዝ ለመንግስት የፀጥታ ሀይል እንድታስረክቡ ጥሪ ያቀርባል፡፡

The post የሃገር ክህደት ወንጀል በፈፀሙ የጁንታው ሕወሓት ቡድን አባላት ላይ የፍርድ ቤት የመያዣ ትዕዛዝ ወጣባቸው appeared first on Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C.

Source: Link to the Post

Leave a Reply