You are currently viewing የህሊና እስረኞች ጉዳያቸው በ እየአካባቢያቸው መታየት እየቻለ ወደ ገንዳውሃ ማምጣት ተገቢ አለመሆኑን በመግለጽ ይህንን ክስ ለማየት የሚያስችል ህጋዊ ስልጣን የለኝም ሲል የገንዳውሃ ፍ/ቤት ው…

የህሊና እስረኞች ጉዳያቸው በ እየአካባቢያቸው መታየት እየቻለ ወደ ገንዳውሃ ማምጣት ተገቢ አለመሆኑን በመግለጽ ይህንን ክስ ለማየት የሚያስችል ህጋዊ ስልጣን የለኝም ሲል የገንዳውሃ ፍ/ቤት ው…

የህሊና እስረኞች ጉዳያቸው በ እየአካባቢያቸው መታየት እየቻለ ወደ ገንዳውሃ ማምጣት ተገቢ አለመሆኑን በመግለጽ ይህንን ክስ ለማየት የሚያስችል ህጋዊ ስልጣን የለኝም ሲል የገንዳውሃ ፍ/ቤት ውሳኔውን አስታወቀ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ታህሳስ 17 ቀን 2015 ዓ/ም አዲስ አበባ ሸዋ የአማራ ወጣቶች ማህበር (አወማ) “የነቁ አማራዎች የፍ/ቤት ውሎ!” በሚል ለአማራ ሚዲያ ማዕከል (አሚማ) የሚከተለውን መረጃ አድርሷል:_ በግፍ እስር የሚገኙት:_ 1) የአማራ ተማሪዎች ማህበር ፕሬዘዳንት እሸቱ ጌትነት፣ 2) ጓደኛው መታገስ ፀጋ፣ 3) የአማራ ህዝባዊ ኃይል (ፋኖ) አመራር ፋኖ ጥላሁን አበጀ፣ 4) የአርበኛ ዘመነ ካሴ አጃቢ የሆነው ፋኖ ናትናኤል እና 5) ኃ/ማሪያም ክብረት ፍርድ ቤት ቀርበዋል። ታህሳስ 17/2015 በገንዳ ውሃ ፍ/ቤት የቀረቡ ሲሆን በስፍራው የሚገኘው ፍ/ቤትም ወንጀል በተፈጸመበት ቦታ ከተማ ፣ ዞን ወይም ወረዳ ሊታይ የሚገባን ክስ በዛው መታየት ሲገባው ገንዳ ውኃ ከተማ እንዲታይ ማድረግ ተገቢነት የለውም በማለት የህሊና ውሳኔ ሰጥቷል። ክብርና ምስጋና ለህሊናቸው ለሚኖሩ ዳኞች ይሁን፤ ይድረሳችሁ። በመሆኑም ይህንን ክስ ለማየት የሚያስችል ህጋዊ ስልጣን የለንም በማለት የፍርድ ሂደቱን ለማከናወን ፈቃደኛ ሳይሆኑ ቀርተዋል፤ የክስ ሂደቱ ተቋርጧል። በግፍ እስር ፣አፈና እና ማወከብ የሚቆም ፥የተጀመረ የአማራ ትግል ፈፅሞ የለም። የትግላችን መዳረሻ የአማራ ህዝብ ነፃነት ነው ። አማራ በቆራጥ ልጆቹ ተጋድሎ ታሪኩን ያድሳል። አማራነት ያሸንፋል።

Source: Link to the Post

Leave a Reply