“የህልውና ዘመቻው ያልተጠናቀቀ ሆኖ ሳለ እንደተጠናቀቀ ተድርጎ መሸፋፈኑ ቆሞ አሁንም በወሎ ፣በጎንደር እና በአፋር ህዝቡ ጦርነት ላይ መሆኑ ታውቆ መንግስት የጽጥታ ሃይሉን እና ህዝቡን በፍ…

“የህልውና ዘመቻው ያልተጠናቀቀ ሆኖ ሳለ እንደተጠናቀቀ ተድርጎ መሸፋፈኑ ቆሞ አሁንም በወሎ ፣በጎንደር እና በአፋር ህዝቡ ጦርነት ላይ መሆኑ ታውቆ መንግስት የጽጥታ ሃይሉን እና ህዝቡን በፍጥነት አስተባብሮ ይህን ጽንፈኛ ሃይል ልንቀብረው ይገባል” ሲል ሸዋ ፋኖ ጥሪ አቀረበ፡፡ አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ጥር 5 ቀን 2014 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ የሸዋ ፋኖ ወቅታዊ ሁኔታወችን አስመልክቶ የተሰጠ መግለጫ! እንደሚታወቀው የአማራን ህዝብ ላለፉት 30 ዓመታት ማህበራዊ ረፍት ተነስቶ ብዙ መከራወችን ሲያስተናግድ የቆየ ህዝብ ነው ትህነግ ከአመሰራረቱ ጀምሮ የአማራን ህዝብ ጠላቴ ብሎ በመፈረጅ የትግል ማንፌስቶ ቀርጾ አማራው ህዝብ ላይ ትልቅ በደል ሲያደርስ ኖሯል አሁንም፡እያደረሰ ይገኛል። ስልጣን ከእጃቸው ከወጣ በኋላ እንኳን ላለፉት ሁለት አመታት በአማራ በማይካድ፤በጭና፤በቆቦ፤በአጋምሳ፤በአንጾኪያ እንዲሁም በአፋር በጋሊኮማ እና የተለያዩ የአማራ ግዛቶች ላይ ትልቅ የዘር ማጥፋት ወንጀል ፈጽሟል፤በተጨማሪም ባለፉት ስደስት ወራት ጦርነት በህዝባችን ላይ ዘግ ናኝ እልቂት እና የንብረት ውድመት ሲፈጽም ቆይቷል። አሁንም የጀመረውን ጦርነት ለተጨማሪ እልቂት አስቀጥሏል፤ ይሁን እና የዚህን የዘር ማጥፋት ወንጀል አቀናባሪዎች፤የጦርነት አቃጅ መሪዎች የተወሰኑትን በህግ ጥላ ስር ማረግ ቢቻልም ለሰሩት ወንጀል ተመጣጣኝ የህግ ቅጣት ያገኛሉ ተብሎ ሲጠበቅ በይቅርታ ሰበብ ክሳቸው ተቋርጦ ሊለቀቁ ችለዋል። ይህም መንግስት ለአማራ ህዝብ ያለውን ንቀት እና ቸልተኝነት የሚያሳይ መሆኑን በግልጽ ያመለክታል። በዚህ ሳይበቃ የሸዋ ፋኖ ሃገር ተወራ መንግስት የክተት አዋጅ ባወጀበት ሰዓት ቅሌን ጨርቄን ሳይል ወራሪውን ሃይል ለማስቆም የአዋጁ ተካፋይ ሆኗል ብዙ ድሎችንም አስመዝግቧል ብዙ ማርኳል ብዙ ምሽጎችን ሰብሯል ብዙ ጓዶችንም አቷል ይሁን እና ይህን መሰዋዕትነት ከምንም ባለመቁጠር ፋኖን እንደ ስጋት መቁጠር ተጀምሯል በመሆኑም የሚከተሉትን ባለ አራት ነጥብ መግለጫ አውጥቷል። 1)ከፊሎቹ የትህነግ ቁልፍ ሰዎች በብዙ ጀግኖች መሰዋዕትነት እና ኦፕሬሽን ካደፍጡበት የአይጥ ጉድጓድ ተይዘው ለፍርድ መቅረባቸው ይታወቃል፤ነገር ግን ለዚህ ሁሉ እልቂት እና ሞት ተጠያቂ የሆኑት እነዚህ ጨካኝ ነቀርሳዎች መንግስት ክሳቸውን ያቋረጠበት መንገድ አሳማኝ ባለመሆኑ በድጋሚ እዲያየው እና ለሰሩት ወንጀል ተመጣጣኝ ቅጣት እንዲያገኙ አጥብቀን እናሳስባለን። 2) ፋኖ በሰላም ቀን አራሽ በጦርነት ተኳሽ የህዝብ አለኝታ እና ደጀን መሆኑ እየታወቀ አንዳንድ የመንግስት አካላት ፋኖን እንደ ስጋት ለመሳል የሚሞክሩ እና ይባስ ብሎ በስምም በግብርም በአላማም ጭራሽ ከማይመሳሰሉ የሰይጣን እና መላዕክት ያህል ልዩነት ካላቸው ጽንፈኛ ሃይሎች ጋር አብሮ ለመፈረጅ የሚደረገው ሙከራ እንዲቆም በጥብቅ እናሳስባለን። 3) ፋኖ የፌደራል እና የክልሉ መንግስት ያቀረቡለትን ጥሪ ተከትሎ እና የክልሉ መንግስት ማርከህ ታጠቅ ብሎ በሰጠው መመሪያ መሰረት ህይወቱን አሲዞ ከጽንፈኛው የትግራይ ወራሪ ሃይል አንገት ለአንገት ተናንቆ እና ማርኮ የታጠቀ መሆኑ እየታወቀ ትጥቅ እናስፈታለን የሚል ሃሳብ የሚአራምዱ አካላት ሃሳቡ ከንቱ እንደሆነ አውቀው ከዚህ ቀቢጸ ተስፋ ሃሳባቸው እንዲታቀቡ በጥብቅ እናሳስባለን፡፡ 4) የህልውና ዘመቻው ያልተጠናቀቀ ሆኖ ሳለ እንደተጠናቀቀ ተድርጎ መሸፋፈኑ ቆሞ አሁንም በወሎ በጎንደር እና በአፋር ህዝቡ ጦርነት ላይ መሆኑ ታውቆ መንግስት የጽጥታ ሃይሉን እና ህዝቡን በፍጥነት አስተባብሮ ይህን ጽንፈኛ ሃይል ልንቀብረው ይገባል፡፡ ከላይ የተጠቀሱትን የህዝብ ጥያቀዎች መንግስት ያለ ምንም ቅድመ ሁኔታ እንዲያስተካክል እና የሃሳብ ለውጥ እንዲያረግ እያሳሰብን ይህ ሳይሆን ቀርቶ የታሰበው ሃሳብ ለመፈጸም እንቅስቃሴ ቢደረግ መንግስት የአማራው ህዝብ የከፈለውን እና እየከፈለ ያለውን መሰዋዕት ከምንም ያልቆጠረው መሆኑን አውቀን የሸዋ ፋኖ ራሱንም ሆነ ህዝቡም ለመጠበቅ የራሱን አካሂድ ለመጓዝ እንደሚገደድ እናሳስባለን። በተባበረ ህዝባዊ ክንድ የመጣብንን የህልውና አደጋ ቀልብሰን ታሪካችንን በደማችን እንጽፋለን። የሸዋ ፋኖ ጥር 2014 ደብረብርሃን

Source: Link to the Post

Leave a Reply