የህብረተሰቡ የመኖሪያ መታወቂያ አገልግሎት ፍላጎት አሁን በሀገሪቱ ባሉ የተለያዩ ሁነቶች ምክንያት የጨመረ በመሆኑ ወረዳዎች ቅዳሜ ሙሉ ቀን እንዲሰሩ መመሪያ መተላለፉን የወሳኝ ኩነት ምዝገባ እና መረጃ ኤጀንሲ አስታወቀ፡፡

ስድስተኛዉ ሀገራዊ ምርጫን ጨምሮ የጋራ መኖሪያ ቤት ዉል እና የማህበር ቤት ምዝገባ በመዲናዋ እየተከወኑ ናቸዉ፡፡በዚህም ምክንያት የመታወቂያ እድሳት እና ምትክ መታወቂያ የሚፈልጉ ተገልጋዮች ቁጥር በከፍተኛ ሁኔታ መጨመሩን በአዲስ አበባ የወሳኝ ኩነት ምዝገባ እና መረጃ ኤጀንሲ በምክትል ዋና ዳሬክተር ማእረግ የኤጀንሲዉ አማካሪ አቶ መላክ መኮንን ለአሀዱ ተናግረዋል፡፡

ካለዉ የመጨናነቅ እና የተገልጋይ ብዛት አንጻር ወረዳዎች ቅዳሜ ግማሽ ቀን ሲሰጡት የነበረዉን አገልግሎት ሙሉ ቀን እንዲሰጡ መመሪያ መተላለፉን ተናግረዋል፡፡በማእከል ደረጃ ባለፉት 15 ቀናት ኔትዎርክ ተቋርጦ የነበረ በመሆኑ ወደ 70 ሺ የሚጠጉ መታወቂያዎችን ቅዳሜ እና እሁድ አትመን ጨርሰናል ወደ ወረዳዎች የማሰራጨቱ ስራም እየተሰራ ነዉ ብለዋል፡፡

ቀን 05/08/2013

አሐዱ ራድዮ 94.3

The post የህብረተሰቡ የመኖሪያ መታወቂያ አገልግሎት ፍላጎት አሁን በሀገሪቱ ባሉ የተለያዩ ሁነቶች ምክንያት የጨመረ በመሆኑ ወረዳዎች ቅዳሜ ሙሉ ቀን እንዲሰሩ መመሪያ መተላለፉን የወሳኝ ኩነት ምዝገባ እና መረጃ ኤጀንሲ አስታወቀ፡፡ appeared first on አሐዱ ራድዮ 94.3 እና ቴሌቪዥን.

Source: Link to the Post

Leave a Reply