የህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት የኮቪድ-19 ምርመራ ለሚከናወንበት ዘመናዊ መሳሪያ የሚሆን ግብዓት ወረፋ እየጠበኩ ነው ሲል አስታወቀ፡፡

ለኮቪድ-19 መመርመሪያነት የሚውሉ መሳሪዎች ግዙፍ በመሆናቸው በዚያው ልክ የሚጠቀሟቸው ግብአቶችም ከፍተኛ መጠን ያላቸው መሆኑን ያብራሩት የኢንስቲትዩቱ ምክትል ዋና ዳይሬክተር አስቻለው አያሌው ናቸው፡፡

እንደ ሀገር የመመርመር አቅማችን አሁን ላይ በቀን 15 ሺህ ብቻ ቢሆንም፤ ከመመርመር ባሻገር መከላከል ላይ ያተኮረ የስትራቴጂ ለውጥ ማድረግ አስፈላጊ ነው ሲሉ ለአሐዱ ተናግረዋል፡፡

አሁን በስራ ላይ ያሉ የመመርመሪያ ማሽኖች ከፍተኛ ግብአት የሚፈልጉ ናቸው፤ ግብአቶቹ ደግሞ ማሽኖቹ ከተገዙባቸው ድርጅት ብቻ የሚገኙ መሆኑ ችግር ፈጥሮብናል ብለዋል ምክትል ዋና ዳይሬክተር አስቻለው አያሌው ለአሀዱ ሲገልፁ፡፡

*******************************************************************************

ዘጋቢ፡ ቤዛዊት ግርማ

ቀን 19/04/2013

Source: Link to the Post

Leave a Reply