You are currently viewing የህወሀት ቡድን በአፋር ክልል ከፍተኛ ግድያ እና ዘረፋ በመፈጸም እያፈናቀለ መሆኑን የክልሉ መንግስት አስታውቋል። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ   የካቲት 10 ቀን 2014 ዓ.ም        አዲ…

የህወሀት ቡድን በአፋር ክልል ከፍተኛ ግድያ እና ዘረፋ በመፈጸም እያፈናቀለ መሆኑን የክልሉ መንግስት አስታውቋል። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ የካቲት 10 ቀን 2014 ዓ.ም አዲ…

የህወሀት ቡድን በአፋር ክልል ከፍተኛ ግድያ እና ዘረፋ በመፈጸም እያፈናቀለ መሆኑን የክልሉ መንግስት አስታውቋል። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ የካቲት 10 ቀን 2014 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ ግድያ እና ዘረፋውን ለመቀልበስ ብርቱ ተጋድሎ እያደረገ የሚገኘው የአፋር ህዝብ ድጋፍ እንደሚያስፈልገው በተደጋጋሚ እየተገለጸ ነው። የክልሉ መንግስት የሚከተለውን ገልጧል:_ የህወሀት ቡድን ከጅምላ እስከ ችርቻሮ ዘረፋ -በአፋር ክልል አሸባሪው ህወሀት ለ 27 አመታት እንደፈለገ የአፋር ክልልን ሀብት ሲመዘብርና ሲያስመዘብር እንዲሁም የክልሉን ፖለቲካዊ፣ ኢኮኖሚያና ማህበራዊ እንቅስቃሴ እንዳሻው ሲዘውር እንደነበር ይታወቃል። በዚህም የአፋር ህዝብ በገዛ መሬቱ የበይ ተመልካች ሆኖ፣ “ለምን? ” የሚል ጥያቄ የሚያነሱ ዜጎችንም የተለያዩ ስያሜ በመስጠት፣ ጎሳን ከጎሳ እንዲጋጭ ቅስቀሳና ሴራ በማድረግ የማራቆት ከፍተኛ ሴራውን ሲሰራ ቆይቷል። ዛሬ ላይም ቡድኑ ለ 27 አመታት አፋርን ሲመዘብር የቆየውን በተደራጀ በሀይል በታገዘ መልኩ ወደ አፋር ክልል ዘልቆ አራት ዞኖች ውስጥ በመግባት የጅምላ ጭፍጨፋ የአፋር ንፁሃን ላይ በመፈፀም፣ ሀብትና ንብረትን በማውደምና በመዝረፍ አሸባሪው ህወሀት አሁንም አፋርን የመመዝበር ህልሙን አጠናክሮ ቀጥሏል። አሸባሪው ህወሀት እንደ አዲስ ወረራ እየፈፀሙ ባሉበት በኪልበቲረሱ ዞን በርካታ ህፃናት፣ ሴቶችና አዛውንቶችን በጅምላ ጨፍጭፏል፣ ከ 300 ሺህ በላይ ዜጎችም ከቀያቸው እንዲፈናቀሉ አድርጓል። በዚህ ወረራም “ህጋዊ” ደብዳቤ ማህተምና ፌርማ ያለው ደብዳቤ በማስያዝ በኪልበቲ ረሱ ወረራ በካሄዱባቸው አካባቢዎች ጨዉ፣ በርበሬ፣ ስኳር፣ ዘይት፣ ፓስታ፣ ማኮረኒ ወዘተ ከአርብቶ አደሩ የዘረፏቸውን አስቤዛ በጅምላና በችርቻሮ ይዘው እንዲመጡ ልከዋል። ሁሌም ከዘረፋ እና ከሌብነት የማይወጣው አሸባሪው ቡድን ህወሀት ዛሬም በወረራ በከባድ መሳሪያ በመታገዝ በጅምላ ከሚጨፈጭፏቸው ንፁሃን ዜጎችና ከቤት ንብረታቸው ያፈናቀሏቸውን ንብረት በመዝረፍ የአፋርን ሀብትና ንብረት ከዚያም አልፎ የአፋርን መሬት ወደ ትግራይ በማካለል “ታላቋን ትግራይ ሪፐብሊክ” የመመስረት ቅዠታቸውን ለማሳካት በአፋር ህዝብ ላይ ከፍተኛ ጉዳት በማድረስ ላይ ይገኛሉ። ታሪካዊው የአፋር ህዝብ ጠላት አሸባሪው ህወሀት የአፋር ህዝብን ለመጉዳት እና መሬቱን ለመቀማት ለበርካታ አመታት ሲያሴር የነበረውን የኢኮኖሚ፣ ማህበራዊና ፖለቲካዊ ሴራ ይፋ በማውጣት ጠላትነቱን ንፁሀኑን በመጨፍጨፍ ፣ ሀብት ንብረቱን ጨውና በርበሬ ሳይቀር በይፋ በመዝረፍ አረጋግጧል። በዚህ በተገኘው ደብዳቤ ዘረፋው የመጀሪያ ሳይሆን ካሁን በፊትም እየዘረፉ እንደሚወሰዱት “እንደተለመደው” በማለት ይገልፃሉ። ቡድኑ ንፁሀንን በ ጅምላ መጨፍጨፍና ሀብት ንብረተ መዝረፉን ተያይዘውታል። የአፋር ህዝብም ወራሪውን ቡድን ወርሮ ያያዛቸውን የአፋር አካባቢዎችን ለማስለቀቅ ብርቱ ተጋድሎ እያደረገ ይገኛል።

Source: Link to the Post

Leave a Reply