የህወሃት ቡድን በቅርሶች ላይ ያደረሰውን ውድመትን ለማወቅ የአጥኚ ቡድን ተላከበተወካዮች ምክር ቤት በአሸባሪነት በተፈረጀው ህወሃት ተይዘው አሁን ነፃ የወጡት አካባቢዎች ላይ በቅርሶች ላይ የ…

የህወሃት ቡድን በቅርሶች ላይ ያደረሰውን ውድመትን ለማወቅ የአጥኚ ቡድን ተላከ

በተወካዮች ምክር ቤት በአሸባሪነት በተፈረጀው ህወሃት ተይዘው አሁን ነፃ የወጡት አካባቢዎች ላይ በቅርሶች ላይ የደረሰው ጉዳት ለማወቅ የአጥኚ ቡድን ወደተለያየ አካባቢ መላኩን የቱሪዝም ሚኒስቴር ሚኒስትር የሆኑት አምባሳደር ናሲሴ ጫሊ ተናገሩ።

ቡድኑ በተለያዩ ቅርሶች ላይ ፣ ብሄራዊ ፓርክ ፣ ሆቴሎች ላይ ከፍተኛ ጉዳት አድርሷል ብለዋል።

ሚኒስቴ መስርያ ቤቱ ቅድመ ጥናት ማድረጉን የገለፁት አምባሳደር ናሲሴ ትክክለኛውን ውድመት ለማወቅ የአጥኚ ቡድን ወደተለያየ አካባቢ መላኩን ዛሬ በሰጡት መግለጫ አንስተዋል።

ትላንት የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ዴዔታዋ ሰላማዊት ካሳ ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ በሽብርተኝነት የተፈረጀው የህወሓት ቡድን ወርሯቸው በነበሩ አካባቢዎች በሚገኙ ቅርሶች፣ የቱሪስት መዳረሻዎች እና ጥብቅ የማህበረሰብ ስፍራዎች ላይ ከፍተኛ ጉዳት መድረሱን ማሳወቃቸው የሚታወስ ነው፡፡

ሚኒስትር ዴዔታዋ ጨምረው እንዳሉት በአማራ ክልል ደቡብ ጎንደር ዞን በቅርስና የቱሪስት መዳረሻ በሆኑ 6 የሃይማኖት ተቋማት፣ 2 የቱሪዝም ድርጅቶች እና በ22 የቱሪዝም አገልግሎት መስጫ ተቋማት ላይ ከፍተኛ ጉዳት፤ ባለሙያዎች ወደስፍራው አቅንተው ባደረጉት ምልከታ ከ23 ሚሊዮን ብር በላይ የሚገመት ንብረት መውደሙም ተረጋግጧል፡፡

ረድኤት ገበየሁ
ህዳር 28 ቀን 2014 ዓ.ም

Source: Link to the Post

Leave a Reply