የህወሃት አባላት በመንግስት የቀረበላቸውን ጥሪ ተቀብለው እጅ እንዲሰጡ የአቶ ጌታቸው ረዳ እህት ጠየቁ!                    አሻራ ሚዲያ…

የህወሃት አባላት በመንግስት የቀረበላቸውን ጥሪ ተቀብለው እጅ እንዲሰጡ የአቶ ጌታቸው ረዳ እህት ጠየቁ! አሻራ ሚዲያ…

የህወሃት አባላት በመንግስት የቀረበላቸውን ጥሪ ተቀብለው እጅ እንዲሰጡ የአቶ ጌታቸው ረዳ እህት ጠየቁ! አሻራ ሚዲያ ህዳር ፡- 16/03/13/ዓ.ም ባህር ዳር የህወሃት ቡድን አባላት በመንግስት የቀረበላቸውን ጥሪ ተቀብለው እጅ በመስጠት የትግራይ ህዝብ ከተጋረጠበት አደጋ ሊታደጉት እንደሚገባ የህወሃት ጁንታ ስራ አስፈጻሚ አባል የሆኑት የአቶ ጌታቸው ረዳ ታናሽ እህት ዋና ሳጅን ትዕግስት ረዳ ገለጹ። እኔ የአቶ ጌታቸው ረዳ እህት ብሆንም የፖለቲካ አመለካከት በዘር አይተላለፍም ብለዋል፡፡ በሰቆጣ ከተማ ለ22 ዓመታት የኖሩት ዋና ሳጅን ትዕግስት ከአሁኑ የሀገሪቱ ወቅታዊ ሁኔታ ጋር ተያይዞ ምንም አይነት ችግር እንዳላጋጠማቸው ገልጸው፤ በመከላከያ ሰራዊት ላይ የተፈጸመውን ጥቃት በጽኑ እንደሚያወግዙት ተናግረዋል። መከላከያ ሀገር ነው፤ ብሔር የለውም ዘር የለውም እሱ እንዲበተን አልፈልግም፤ ሀገርን የሚጠብቅ ሰው ሲሞት በጣም አዝኛለሁ ያሉት ዋና ሳጅን ትዕግስት ረዳ፤ መንግስት እያካሄደ ያለው የህግ ማስከበር ዘመቻ ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት ገልጸዋል። የህወሃት ከፍተኛ አመራሮች የግል ጥቅማቸውን ለማስጠበቅ ሲሉ የትግራይን ወጣት ለጦርነት መማገዳቸው ለትግራይ ህዝብ ደንታ እንደሌላቸው ማሳያ እንደሆነም ጠቅሰዋል። በወንጀል የሚፈለጉ የህወሃት አመራሮች በሰላም እጃቸውን እንዲሰጡ ለሁለተኛ ጊዜ በመንግስት በኩል የቀረበላቸውን የሰላም ጥሪ በመቀበል ህዝባቸውን ከተጋረጠበት አደጋ ሊታደጉት ይገባል ብለዋል። ዘጋቢ፡- ጥላሁን ታምሩ

Source: Link to the Post

Leave a Reply