የህወሃት የጥፋ ቡድን በማይካድራ የፈፀመውን አይነት እኩይ ተግባር በመቀሌ ለመድገም እየተንቀሳቀሰ መሆኑን ኮሚሽኑ ገለፀ

አዲስ አበባ ፣ ህዳር 17 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የህወሃት የጥፋ ቡድን በማይካድራ የፈፀመውን አይነት እኩይ ተግባር በመቀሌ ለመድገም እየተንቀሳቀሰ መሆኑን የፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን ገለፀ፡፡

ኮሚሽኑ የቡድኑ እኩይ ዕቅድ መረጃ እንደደረሰውም አስታውቋል፡፡

በትግራይ ክልል የተጀመረው ሕግን የማስከበር እርምጃ ሁለተኛ ምእራፍ ተጠናቆ የመጨረሻውና ሦስተኛው ወሳኝ ምዕራፍ ላይ መድረሱንም ገልጿል፡፡

ይህ በዚህ እንዳለ ፅንፈኛው የህወሃት ጁንታ ቡድን መቀሌ ከተማ ውስጥ የሚኖሩ የትግራይ ተወላጆች ያልሆኑት ሰዎች ላይ አሰቃቂ ግድያ ለመፈፀም፣ ንብረታቸውን በመዝረፍ ለማቃጠል፣ የመከላከያ ሠራዊት የደንብ ልብስ በመልበስ ሰዎች ላይ በድንገት ተኩስ በመክፈት አስነዋሪ ድርጊት ለመፈፀም ማቀዱን ደርሼበታለሁ ብሏል፡፡

ቡድኑ ሰሞኑን በማይካድራ የፈፀመውን አስነዋሪና አሰቃቂ ጭፍጨፋ ለመድገም እቅድ አውጥቶ ተግባራዊ ለማድረግ እየተንቀሳቀሰ መሆኑንና ይህንን እኩይ ተግባር ከፈፀመም በኋላ ድርጊቱ የተፈፀመው በመንግስት ነው ብሎ በሚዲያ ለማሰራጨት የተዘጋጀ መሆኑን ከህዝብ መረጃ ደርሶኛል ነው ያለው ኮሚሽኑ።

በመሆኑም ሁሉም ኢትዮጵያዊ እና ዓለምአቀፍ ማህበረሰብ ይህንን የጥፋት ሴራ ተከትሎ ጁንታው ቡድን ሊያሰራጭ የተዘጋጀውን የሃሰት ፕሮፖጋንዳና ይህንን እኩይ ተግባር አስቀድሞ እንዲረዳና ተቀባይነት ያጣ ዘንድ የበኩላችሁን ጥረት እንድታደርጉ ማሳሰብ እንወዳለን ሲል አስውቋል።

ህዝቡ ማንኛውንም የተለየ እና አጠራጣሪ እንቅስቃሴ ሲያይ ለፀጥታ አካላት ጥቆማ እንዲሰጥ ጠይቋል፡፡

The post የህወሃት የጥፋ ቡድን በማይካድራ የፈፀመውን አይነት እኩይ ተግባር በመቀሌ ለመድገም እየተንቀሳቀሰ መሆኑን ኮሚሽኑ ገለፀ appeared first on Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C.

Source: Link to the Post

Leave a Reply