የህወሃት ጁንታ የሀሰት ፕሮፓጋንዳና የጦርነት ቅስቀሳ ሲያደርግበት የነበረውን ሬዲዮ ጣቢያ ዘርፎና አውድሞ ሸሽቷል

አዲስ አበባ ፣ ህዳር 26 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የህወሃት ጁንታ የሀሰት ፕሮፓጋንዳና የጦርነት ቅስቀሳ ሲያደርግበት የነበረውን ድምጸ ወያኔ ሬዲዮ ጣቢያ ዘርፎና አውድሞ ከመቀሌ ከተማ መውጣቱ ታውቋል።
የሰራዊቱን ፈጣንና የተቀናጀ እርምጃ መቋቋም ያልቻለው ቡድን ”እኔ ከሞትኩ ሰርዶ አይብቀል” እንደሚባለው ከፊት ለፊቱ ያገኘውን የህዝብና የመንግስት ንብረት እየዘረፈና እያወደመ ሸሽቷል።
በተለይም በህዝብ መገልግያ መሰረተ ልማቶች በትምህርት ቤቶች፣ በጤና ጣቢያዎች፣ በመንገድ፣ በድልድይና በኤርፖርቶች ላይ ያደረሰው ጥፋት ጸረ-ህዝብነቱን በግልጽ ማሳየቱም ተገልጿል።
ቡድኑ ፕሮፓጋንዳና የጦርነት ቅስቀሳ ሲተላለፍበት የነበረው የድምጸ ወያኔ የስርጭት ጣቢያ የህዝብ ንብረት ቢሆንም ‘እኔ ካልተጠቀምኩበት’ በሚል በስቱዲዮ የሚገኙ ንብረቶችን ዘርፎ የቀሩትን አውድሞ መሸሹ ተነግሯል።
የሀሰት ፕሮፓጋንዳ በማስተላለፍ ህዝብን ከሚያደናግርባቸው መገናኛ ብዙሃን መካከል ድምጸ ወያኔ፣ ትግራይ ሬዲዮና ቴሌቭዥን እንዲሁም ወይን ጋዜጣ ተጠቃሽ ናቸው።
በመከላከያ ሰራዊት ቁጥጥር ስር የዋለውን ጣቢያ የመገናኛ ብዙሃን ባለሙያዎች በስፍራው ተገኝተው መመልከታቸውን ኢዜአ ዘግቧል።
የአገር መከላከያ ሰራዊት መቀሌ ከገባ በኋላ ከተማዋ ወደ ሰላማዊ እንቅስቃሴ እየተመለሰች ትገኛለች።
ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

The post የህወሃት ጁንታ የሀሰት ፕሮፓጋንዳና የጦርነት ቅስቀሳ ሲያደርግበት የነበረውን ሬዲዮ ጣቢያ ዘርፎና አውድሞ ሸሽቷል appeared first on Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C.

Source: Link to the Post

Leave a Reply